
ግብዙ የምዕራባዊያን ‘ጆሮ ዳባ’ ለአል ቡርሐን የይሁንታ መብራት ሆኗል
✍️ Esleman Abay [የዓባይልጅ]
ለጀነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሐን ዋነኛው ወታደራዊ አቅማቸው የነበረው የሱዳን SAF አየር ኃይል ማዘዣ ከእጃቸው ወጥቷል። አሁን በሔሜቲ RSF ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል። ይህ ሽንፈት በተለይም ለካይሮው አል ሲሲ እና ለአገልጋዩ ጀነራል አል ቡርሃን የፍፃሜ መጀመሪያ እየተባለ ይገኛል። ይሁንና አል ቡርሃን ቁልቁለቱን በህገወጥ ጥቃት ታጅበው ለመውረድ የመረጡ ነው የሚመስሉት።
በካይሮ የሚታዘዘው የአል ቡርሐን SAF ጦር በዓለም አቀፍ ህጎች የሚከለከሉ ወታደራዊ ርምጃዎችና ጥቃቶችን እየሰነዘረ ይገኛል።
ይህ የሱዳን (ወታደራዊ ክንፍ) SAF ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ RSF ሃይሉ ተደብቆባቸዋል በሚል ሽፋን በካርቱም በሚገኙ የአምስት ሀገራት ኤምባሲዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል። ለነዚህ የአየር ድብደባዎች ሽፋን የሚያደርጉ አውሮፕላኖች ከግብፅ በድጋፍ መልክ የተሰጡ ሲሆኑ፤ የአል ቡርሐንን ወታደራዊ ጥቃት እየደገፉ የሚገኙ የግብጽ አውሮፕላኖች መሆናቸው መታወቅ የሚገባው ነው።
ግብጽ ይህንን ተግባር እየፈጸመች የምትገኘው በተለይም ከሄሜቲ ጀርባ ተሰልፈው ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል የምትጠረጥራቸው ሀገራትን ለማስጠንቀቅ አሊያም በትኮሳዋ ወደ ጦርነቱ ለመጎተት መሆኑ ይታመናል። መሰል ዓለም አቀፍ የጦርነት ህጎችን የሚጥሱና በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ድርጊቷን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኃላፊነት የሚሰማው ከሆነ ድርጊቱን ሲያውግዘው ልንመለከተው የተገባ አንድ ርምጃ ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሚገራርሙ ሁነቶች፤
▪️የግብፅ አየር ኃይል የሱዳኑ ጦርነት በሚያዚያ አጋማሽ ሲቀሰቀስ በቀጥታ የውጊያ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ይህንንም ካይሮ እንደ ህጋዊ ርምጃ ነበር በይፋ እወቁልኝ ያለችው።
???? በሱዳን እየተዋጉ የሚገኙት ጊዜያዊ የሽግግር ስልጣናቸው መገባደጃ ላይ የነበሩ ሁለት የወታደራዊ ክንፍ መሪዎች ናቸው። በሁለቱ መካከል “መፈንቅለ-መንግስት ተደረገ” የሚያስብል ህጋዊ መሰረት ሊኖር አይችልም። ይልቁንም “የሱዳን ሽግግር ሂደት እንቅፋት እገጠመው” በሚል ነው አሳዛኙ ቀውስ ሊገለፅ የሚችለው። ታዲያ በመሰል ቀውስ ውስጥ አንዱን ህጋዊ ሌላኛውን ፈንቃይ አድርጎ መደገፍና መተቸት የምዕራባዊያን የተለመደ ግብነት (Double Standard, Hypocrisy) መሆኑን ሁሉም ያውቀዋል።
▪️አለም አቀፉ ማህበረስብ የግብፅ አየር ኃይልን ጣልቃ ገብነት አላወገዘም። በተቃራኒው ኢትዮጵያንና ኤርትራን በመላምታዊ ትንታኔ ላይ ብቻ ተመስርተው እጃቸውን አስገብተዋል የሚል ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ ነው የሚስተዋሉት።
????ከህወሃት ጋር በተደረገው ጦርነት የኤርትራ ጦር ያደረገውን ወታደራዊ ተሳትፎ ሲያወግዙ ከአዲስ አበባ በላይ ለሀገሪቱ ተቆርቋሪዎች ለመምሰል ሲተውኑ እንደነበር አይዘነጋም።
????የግብፅ አየር ኃይል በካርቱም የሚያደርገውን ውጊያ በይሁንታ ተቀብሎ የሩሲያውን የግል ወታደራዊ ተቋራጭ Wagner ተወቃሽ ማድረግ ጤነኝነት ነውን..? እንደውም ዋግነር ከሁለቱም ጀነራሎች (ከአል ቡርሐን እና ከሔሜቲ ጋር በጋራ በተፈረመ ስምምነት መሰረት ነው በሀገሪቱ እነቅስቃሴ ማድረግ ሐጀመረው።
▪️በሱዳኑ የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ አሜሪካ እና ግብፅ ኢዲስ አበባ ለሔሜቴ ድጋፍ እያደረገች ነው በሚል ዘመቻ ተከስተው ነበር። ቀጥሎ የሆነው ደግሞ የሄሜቲ ጦር በካርቱም የአውሮፓ ህብረት ቢሮ እንዲሁም የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ፈፀመ የሚል ወቀሳ ነበር። በተከታይነት ደግሞ በካርቱም የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ነበር። ለዚህ ጥቃት ቀድመው ምላሽ የሰጡት አስመራ ወይም አዲስ አበባ አልነበሩም። ይልቁንም ምዕራባዊያን ድርጊቱ በድጋሚ የሔሜቲን RSF ነበር ተወቃሽ ያደረጉት።
????አዲስ አበባ እና አስመራ ለ RSF ድጋፍ እያደረጉ ከሆነ ይኸው የሔሜቲ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል ስለምን የኢትዮጵያ እና የአስመራ ኢምባሲዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል….።
የምዕራባዊያኑ ባይደናም ፕሮፓጋንዳ ራሱን መከላከል ተስኖት ፍጥጥ ብሎ ከአደባባይ እየዋለ ይገኛል። በሱዳኑ ቀውስ ኢትዮጵያ የተከተለችው ፖሊሲ የካይሮን የቀውስ ቀመር አርክሶታል። አል ሲሲ ዘለው የተነከሩበት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ያሰቡትን የኢትዮጵያ ተሳትፎ ማጣቱ በተከታይነት ላለሙት የውጥንቅጥ ቢጋራቸው መግቢያውን ብቻ ሳይሆን የመውጫ በሩንም የዘጋባቸው ይመስላል።
ሠላም ለሱዳናዊያን
Esleman Abay #የዓባይልጅ