Deprecated: Creation of dynamic property OMAPI_Elementor_Widget::$base is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/optinmonster/OMAPI/Elementor/Widget.php on line 41

የግብፁ GIS ደህንነት ተቋም ለህወሃት ጦርነት የሚሊዮን ዶላሮችና ተከታታይ ድጋፍ ስምምነት ከደህንነት ምንጮች ተሰማ

የዓባይ፡ልጅ

የግብፅ ደህንነት ጠቅላላ አገልግልት General Intelligence Service- GIS ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበት እንዲሁም ከግድቡ 3ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ጅማሮ በፊት የተለያዩ የኢትዮጵያ ታጣቂ ኃይሎችን ስምሪት እንዲሰጥ፣ በዚህም የግድቡ ግንባታ ሂደት ይስተጓጎል ዘንድ ከግብፅ መንግሥት ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ነው ምስጢራዊ መረጃውን ያጋለጡ ምንጮች ለሚመለከተው አካል ባደረሱት መረጃ የጠቆሙት።

የግብፁ የደህንነት መስሪያ ቤት ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና በሦስተኛው ዙር የህዳሴ ግድቡ ሙሌት ማስተጓጎል ጋር ለተያያዘው ተልዕኮ 2 ሚልዮን ዶላር እንዳበረከተለትና በዬ 45 ቀኑም 500 ሺ ዶላር ድጋፍ ሲያደርግለት የደህንነት ምንጮች በዛሬው እለት ባደረሱት መረጃ የተገለፀው።

የግብፅ ጠቅላላ የመረጃ አገልግልት General Intelligence Service- GIS ቦርድ ኃላፊ ብ/ጀነራል ሙታዝ ሙስጠፋ እና የአፍሪካ ላይዘን ኃላፊ ብ/ጀነራል ሙስጠፋ ማርዋን 2 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በዲፕሎማሲያዊ ሂደት ወደ ሱዳን ካስገቡ በኋላ በካርቱም ለሚገኙ የሽብር ቡድኑ ተወካዮች ማስረከባቸውን የሚያጋልጡ የሰነድ ማስረጃዎች የተገኙ ሲሆን፤ ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና በኢትዮጵያ አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል በየ45 ቀኑ 500 ሺ የአሜሪካ ድላር ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡
ሱዳን እና ግብፅ ህወሓትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግሥትና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ሁኔታውን ለመቀየር ያላቸውን ፍላጎት ለማሳካት ለአሸባሪ ቡድኑ የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክ፣ የስልጠናና ሌሎችም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይም ግብፅ የሽብር ቡድኑ የመንግሥት ለውጥ ማምጣት ባይቻል እንኳን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎችን በማቀናጀት የህዳሴ ድግቡን የ3ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉል ከፍተኛ ተስፋ አድርጋ የነበረ ሲሆን፤ የትግራይ ክልል ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮችም የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገላቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ እንደሚያከናውኑ ተስማምተው እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Esleman Abay✍️ #የዓባይልጅ

Share:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

VK Russian online social media and social networking service
Categories