ሞስኮን ከጉባ ያገናኘው የዋሽንግተን ሴራ


እስሌማን ዓባይ

የሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት በግድባችን ጉዳይ ይመጣል የሚል ግምት በስፋህ ይኖር ዘንድ መጠበቅ ላያስፈልገን ይችል ይሆናል። ዛሬ ላይ ሆነን፤ ያኔ ሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻዋን በዩክሬይን በጀመረችበት ወቅት “አርፋችሁ ተቀመጡ” የሚሉ ድምፆች እዚሁ ከሚገኙ ዜጎች ሲዘነዘር ነበር። ያንን ብልጣብልጥ የተኩላ ምክር ዛሬ ላይ በትውስታ ብቻ የምናነሳው አይደለም። ይልቁንም “ልሙጥ ገለልተኛ ሁኑ” ሲሉን ከነበሩት ውስጥ የተወሰኑት አንድም አስበውበት/ሲቀጥልም ተልእኮ ተቀብለው እንደነበር ማሳያዎች ወገግ ይሉ ጀምረዋል። ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚያንፀባርቁትን አተያይ/opinion ምእራባዊያን በዚህ ደረጃ ዋጋ ሰጥተው ባንዳ ለማሰማራት ያበቃቸዋል ወይ? የሚል ጠያቂ እንደማይኖር ልገምት። ድንገት ከመጣም ጥያቄውን በጥያቄ ለመመለስ “የዲጂታል ዘመቻን እየመረጡ ሲያፍኑ ኢትዮጵያዊ ድምፆች ላይ ብሎም የሩሲያ ደጋፊ ሀሳቦችን ጭምር መሆኑ ከምን የመነጨ ይመስልሃል?” ብቻ ማለት በቂ ነው።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አለመግባባትን ለመፍታት ሶስቱ ሀገራት ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን ላለፉት ሁለት ወራት በአቡዳቢ ድርድር ሲያደርጉ መቆየታቸው ተሰምቷል። ስለዚሁ ጉዳይ ከወራት በፊት የወጡ ዘገባዎችን ማጋራቴ ይታወሳል። በወቅቱ የሶስትዮሹን የካይሮ ኢኒሼቲቭ ሱዳን እንጂ ካይሮ አሻፈረኝ ማለቷ ነበር የተዘገበው። የማታ ማታ ግን የአቡዳቢም ጥያቄ ተቀብላ እድሏን ስትሞክር መቆየቷ አሁን ላይ ይፋ ሆኗል።

የግብፅ ብዙሃን መገናኛ የሆነው ማርሳድ እንዲሁም አልአረቢ የተለያዩ ባለስልጣናትን በማነጋገር ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት በአቡዳቢ ሸምጋይነት በህዳሴ ግድቡ ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረው ድርድር ያለ ስምምነት ተቋጭቷል ነው ያለው።

አልአረቢ ከግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮቼ የሰማሁት ነው በማለት እንዳስነበበው ሲል የካይሮ ልዑካን በአቡዳቢ ቆይታቸው የተለመደውን አስገዳጅ ስምምነት ኢትዮጵያ ትፈርም ዘንድ ሲሞግቱ ነበር። ይሁንና በሁለት ዙር ሁለት ወራት ውስጥ በተካሄደው ድርድር ኢትዮጵያ የግብፅን ጥያቄ አሁንም ውድቅ አድርጋለች። ከዚህ ባሻገርም ግብፅ ስለ ግድቡ ሙሊት መረጃ ከኢትዮጵያ ይደርሳት ዘንድ ጠይቃ ነበር። በተጨማሪም የግድቡን ሙሉ ዲዛይን በማቅረብ ስለ ግድቡ ደህንነት ለመምከር አጀንዳ አስይዛ ነበር። ይሁንና ኢትዮጵያ ስለ ሶስተኛው ዙር ሙሊት ብቻ መረጃ እንደምትሰጣቸው መግለጿ ተዘግቧል። በተረፈ በግድቡ ደህንነትም ሆነ ዲዛይኑን በተመለከተ መረጃ እንደማትሰጥ ለግብፅ ልኡካን አስረግጣለች ነው የተባለው።

የአቡዳቢው የድርድር ሂደት በተመለከተ ካይሮ ለዋሽንግተን ማብራሪያ እግር በእግር ስታደርስ መቆየቷን ያስነበቡት አልአረቢ እና ማርሳድ የአቡዳቢው ድርድር ባለመስማማት መቋጨቱን ተከትሎ ግብፅ ለዋሽንግተን ባለስልጣናት አቤቱታቸውን ማሰማታቸው ነው የተነገረው።
በዚህም የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ለሆኑት ጃክ ሱሊቫን በቅርቡ ማለትም ግንቦት 11 2022 ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ፕሬዚዳንት አልሲሲ በቀጣይ ሰኔ አጋማሽ ይቀጥላል በተባለው ሶስተኛ ዙር የአቡዳቢ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ ግትር አቋሟን እንድትቀይር ብሎም አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም ዋሺንግተን ከፍ ያለ ጫና ታደርግ ዘንድ መጠየቃቸው ተነግሯል። በምላሹ ጃክ ሱሊቫን ግብፅ በግድቡ ድርድር የጠየቀችውን ፍላጎቷን ዋሽንግተን ትረዳት ዘንድ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና መከለስ አለባት ብለዋቸዋል።
በነገራችን ላይ ግብፅ በሩሲያ ዩክሬይን ጉዳይ ወደ አሜሪካ በተወሰነ ደረጃ ደግሞ ገለልተኛ ለመምሰል የሞከረ አቋም ስታሳይ እንደነበር ይታወሳል። በሌላ በኩል ባለፈው ክረምት የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ ህዳሴ ግድብ አጀንዳ ባካሄደው ጉባኤ ሩሲያ ኢትዮጵያን በመደገፏ ካይሮ ከሞስኮ የነበራትን የኑክሌር ልማት ስምምነት እንዲቋረጥ ማድረጓም አይዘነጋም። ይሁንና ካይሮ ከሩሲያ የጀመረችውን የኑክሌር ግንባታ ለመቀጠል ከወር በፊት በሚያዚያ ወር ምክክር ያደረገችው በዩክሬይኑ ቀውስ መሀል መሆኑ እዚጋ ታሳቢ ይሆናል።

ዋሽንግተን የዩክሬይኑን ካርታ በህዳሴ ግድቡ በኩል ካይሮን ልትጫወታት በሞከረችበት “የማይከበር ቃል ኪዳኗ” ተከታዩን የሞት አማራጭ ነበር ግብፅ እንድትቀበል የጠየቀችው። ይኸውም የደህንነት አማካሪው ጄክ ሱሊቫን “ካይሮ ከሞስኮ ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማቋረጥና ሩሲያ በዩክሬይን የምታደርገውን ዘመቻ አውግዛ የአሜሪካን አቋም ሙሉ በሙሉ መደገፍ አለባት።” ሲሉ ለአልሲሲ መናገራቸውን የግብፁ የመረጃ ምንጭ አስፍሯል።

እስሌማን ዓባይ #የዓባይልጅ

References ⬇️

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories