ነገረ በርበራ

ስለ በርበራ አልደነቅም። ጉዳዩ አጠገባችን የተሰነቀሩ መርጦ ወጊዎች እየተነሱ “በርበራ በራች፤ በርበራ ጠፋች” እንደሚሉት ስላልሆነ..። የቀጣናው ተጨባጭ (በአመዛኙ) የአለም አቀፉ ተለዋዋጭ ጂኦፖለቲካዊ ውሽንፍር ነፀብራቅ ይሆን ከጀመረ ሰንባብቷልና።

የኢትዮጵያ 19 በመቶ የበርበራ ወደብ ድርሻ አይቀሬ የሚያደርጉት ብዙ ምክንያት ናቸው። ዲፒ ወርልድ ወደቡን ሊያለማ ሲነሳ ኢትዮጵያ የተሰጣት ድርሻ በሱ በዲፒ ወርልድ ፍላጎት ሳይሆን በሃርጌሳ ጋባዥነት ስለመሆኑ አልፎ አልፎም ቢሆን መገለፁ ተያይዞ ሊወሳ ይችላል።
በአንዲት ወር ጊዜ ውስጥ የታዩ ተለዋዋጮች የኛዎቹን የባእዳን ተላላኪ ሸለምጥማጦች ማስክ መገላለጡ ግን ለኔ አስደስቶኛል። ትላንት officiall ያልተደረገ ምንጭን ዋቢ አድርገው የዲፕሎማሲ ኪሳራ ያሉ ጭንቅላቶች ዛሬ ላይ ደግሞ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት የሚል ዋልታ ረገጥ ድምዳሜ የሚጠቁመን ሰዎቹ ከቀይ ባህር በበረታ የህሊና ወጀብ መሀል መሆናቸውን ነው። ታዲያ ይህ ካልሆነ የዛሬ ወር ላይ በአፍሪካ ቀንድ ጂኦፖለቲካ ላይ ከሰረ ሲሉ ለባእዳን ተልእኳቸው ማሟያ ያደረጉት ድምዳሜ በዚህ አጭር ጊዜ እንዴት ወደ ስኬት እምደተገለበጠ ማሳያ ኖሯቸው አይደለም። ማፈሪያ ቢስ በሏቸው።
የሆነ ሆኖ፣ የሶማሊላንዱን በርበራ ወደብ ጂቡቲ ጥቅሟን እንደሚጎዳ አድርጋ ታየዋለች። ኢማራት በዶራሌህ ወደብ ለጂቡቲ ያቀረበችው ፕሮፖዛል ውድቅ መሆኑን የተከተለ ነው ዲፒ ወርልድ በሶማሊላንድ መልህቁን የጣለው።


በርበራ ወደብ ከኢትዮጵያ የወደብ አመታዊ ፍላጎት ግማሽ ያህሉን ያስተናግዳል መባሉ የኢትዮጵያን 95 በመቶ ስታስተናግድ በምትገኘው ጂቡቲ ላይ የሚፈጥረው የገቢ መቀነስ ብቻ አይደለም። የበርበራ ወደብ በቻይና belt and road ፈንድ የተገነባው የኢቲዮ ጂቡቲ ባቡር ላይም ጉልህ ተፅዕኖ ያሳርፋል የሚሉ እሳቤዎችም አሉ።
ሶማሊላንድ አሁን የሀገረ መንግስትነት እውቅናን አጥብቃ ትፈልገዋለች። አሜሪካ ለሶማሊላንድ ሉአላዊ ሀገርነት እውቅና ያበራችው አረንጓዴ መብራት ወደ ቀይ ተቀይሯል። ዋሽንግተን ሀርጌሳን ገፍትራ ከሞቃዲሾ ወረት ላይ ናት። ፑቲን በሶማሊላንድ ወታደራዊ ቤዝ ለማቋቋም እስከ ፈረንጆቹ 2018 ድረስ ቅድመ ስራዎችን ሲያከናውን ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ሶማሊያ ስጋቷ እንኳን ሞስኮ የተባበሩት አረብ ኢማራት ወደ በርበራ መግባቷን ለተመድ አቤት እስከማለት አድርሷታል። በተለይም የኢማራት ወታደራዊ ኮቴ በሶማሊያ እንዳይመጣብኝ ስትል በገለፀችው ስጋቷ…። በቅርቡ ደግሞ ሰርክ በምእራባዊያን ሲሾር የአለም የጉልበት ሚዛን ከቅርብ አመት ወዲህ ሲሰነጣጠቅ ቆይቶ ዩክሬይን ላይ ፑቲን ቀብሩን አድርጎታል፤ ይህንኑ ድምዳሜ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ለCBS ከሶስት ቀናት በፊት የገለፁት ነው። ይህን ተከትሎ ቻይና መር የሆነው ብሪክስ ጡንቻውን ማፍታታት ጀምሯል። በትሪሊዮኖች ዶላር የራሱን ባንክ ስለመጀመሩ ተነግሯል። አለም ባንክን ያስከነዳዋል እየተባለለት ነው። ሳይጠቀስ የማይታለፈው የቻይና እና ታይዋን መጨረሻ ነው። ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ታይዋንን ወደ ነባር አንድነቷ ለመመለስ ወደ ፈፅሞ ኋላ የለም፤ እምቢ የሚል አደናቃፊ ከመጣ ያለንን ሁሉ ጉልበት ከመጠቀም አናፈገፍግም” ማለታቸው የታይዋን እጣ ፋንታ ወዴት እንደሚያመራ ጠቋሚ ነው የሚሉ እየተበራከቱ ይገኛል።
ታዲያ እነዚህ ሁሉ ተለዋዋጭ አለማቀፍ ክስተቶች በአፍሪካ ቀንድ የሚኖራቸው ተፅእኖ ጫን ያለ ይሆናልና፤ ምናልባትም ሶማሊላንድ የሉአላዊ ሀገርነት እውቅናውን ከአሜሪካ መጠበቅ ላያስፈልጋት ወይም ደግሞ እውቅና የመስጠቱ ሚዛን እየፈረጠሙ በመጡ ነብር ወታደረ-ኢኮኖሚዎች ሊነጠቅ ይችል ይሆናል፤ አሊያም ጉዳዩ በአዲስ አለም አቀፍ ‘ነገረ-መርህ’ የሚስተናገድበትን ትእይንት እንመለከትም ይሆናል። ጅምሮችም እየታዩ ስለሆነ፤ ቻይና ያስጀመረችው horn africa peace conference ከብዙዎቹ አንዱና ዋነኛው ነው።
ለዚህም ነው የሶማሊላንድ ጉዳይ እኛ እዚህ ሀገር ውስጥ በዘር እንደምንቦጫጨቀው አይደለም የምለው፤ ነገረ-ሀርጌሳ የምእራባዊያን ተላላኪዎች ከሚያሯሩጡ ባንዳዎች ወሬ የተለየ ነው ከሚያስብለኝ ውስጥም አንዱ ይኸው ነው። የቀንዱ ንቅ-ገሞራ ገና አልሰከነም፤ ብዙ መንተክተክ የሚጠብቀውም ይመስላል። የሶማሊላንድ ጉዳይ ገና ነው።
ከቪላዲሚር ፑቲን ዘመቻ-ዩክሬይን በመቀጠል ቤይጂንግ “ፕሮጀክት-ታይዋን” ላይ የሀሳቧ ከሞላላት ያኔ የሀገሬ ልጆች አንድ ነገርን ጠብቁ። ምን እንጠብቅ ብትሉኝ አሁናዊ መልስ ማምጣት ባልችልም..ነገሮች ግን ከአንድ የሀገራችን ዝነኛ አባባል ጋር የሚገጥም ይመስለኛል…፤ አባባሏ ደግሞ
“ወደ ምስራቅ ተመልከቱ..!”

እስሌማን ዓባይ Esleman Abay

HornOfAfrica #Berbera #Ethiopia #Somaliland

የዓባይልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories