አስቸኳይ የሕግ ማዕቀፍ ለጣና

Ramsar law for lake tana

first published june 2020

በአለም ዙሪያ አደጋ የተጋረጠባቸው የውሀ አካላት እንዲያገግሙ ከአለማቀፍ አጋሮች በቢሊዮኖች ዶላር ፈንድ እየተደረገላቸው ይገኛል። ፈንድ ማግኘት የቻሉት በዋናነት በ Ramsar Site ዝርዝር ውስጥ በመካተታቸው ነው።

ራምሳር የውሀ አካላትን አደጋ ለመቅረፍና ለመንከባከብ በ UN ደረጃ የተቋቋመና 1975 ወደስራ የገባ ነው። አገራትና አለማቀፉን ማህበረሰብ አስተባብሮ ርጥበታማ ቦታዎችን የመንከባከብ ተግባርን ያሳልጣል።

“የአካባቢው ነዋሪዎች ርጥበታማ ቦታዎች ለወባ ትንኝና ለሌሎች በሽታዎች መፈጠሪያ እንደሆነ ተደርገው ይወሰዳሉ። ለተፈጥሮ ሚዛን፣ ለብዝሀ ህይወት፣ ለሀይቆች እንዲሁም ለውሀ አካላት ያለውን ፋይዳ አልተረዱትም። መንግስትም ግንዛቤውን አልፈጠረም…” የሚለው ምኑየለት መንግስቴና ኢብራሂም ሙሀመድ የተባሉ ምሁራን 2018 ላይ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ያቀረቡት ምርምር ነው። ጥናቱ “የአካባቢን ጉዳይ የሚመሩ ባለስለሰጣናትም ስለ ርጥበታማ ቦታዎች ፋይዳ እውቀቱ የሌላቸው ናቸው” ሲል ይጨምራል።

እውነታው ግን ጥቂቱን የአለማችንን ቆዳ ስፋት የሚይዙት ርጥበታማና ረግረጋማ ቦታዎች 40 በመቶውን የአለም ስነ ምህዳር የሚፈጥሩት እነሱ ናቸው። ያለነሱ ብዝሀ ህይወት፣ የሀይቅና ወንዞች ኦርጋኒክ ይዘት፣ ለም ማዕድናት ወዘተ… አይታሰቡም።

በ Ramsar wetland site ዝርዝር ውጥ መካተት የቻሉ የውሀ አካላ ታዲያ የድጋፉ ተጠቃሚ ሆነዋል። እስከ 2018 ድረስም 2,231 የራምሳር ሳይቶች ተመዝግበው የጥበቃና እንክብካቤ ፕሮጀክት አግኝተዋል። ሳይቶቹ 169 አገራት የሚገኙ ሲሆኑ በድምሩም 2.1 ሚሊዮን ስኩ.ኪ.ሜትር ስፋት የሸፈኑ ርጥበታማ ቦታዎች ናቸው። ራምሳር wetland ብሎ የሚለያቸው ሀይቆች፣ ወንዞች፣ ረግረጎች፣ የባህር ዳርቻዎች፣ ሰው ሰራሽም ሆኑ የተፈጥሮ የውሃ አካላት ሲሆኑ ባላቸው ማህበረ ኢኮኖሚና የአካባቢ አበርክቶ ካለባቸው የስጋት መጠን ጋር ተለክቶ ይመረጣሉ።

የጣና ሀይቅም ይህን የራምሳር መስፈርት እያሟላ ነገር ግን በአለም ከ 2300 በላይ ሳይቶች ውስጥ እንዲመዘገብ አልሆነም። በአለም ላይ ከተመዘገቡት ከ 2300 በላይ ሳይቶች 40 በመቶው በአፍሪካ ናቸው። ጎረቤት ኬንያን ብንጠቅስ 6 ሳይቶችን አስመዝግባለች። የውሃ ማማ የባለችው ኢትዮጵያ በአየር ንብረት አለማቀፍ ዘመቻው ላይ የአፍሪካ እንደራሴ ብትሆንም አንድም የውሃ አካልን ማስመዝገብ አልቻለቸፈችም። ለምዝገባው የሚያስፈልገው የውሀ አካላትን መረጃ ሰንዶ ለራምሳር ሪፖርት ማድረግ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ከ ramsar convention ጋር የሚጣጣም ህቅ አርቅቆ ማፀሸደቅ ነው። ነገር ግን እስካሁን አልተደረገም።

በኢትዮጵያ ሰፊ ርጥበታማ ሀብቶችአሉ።” Forum for Environment 2009 ላይ ያወጣው ሪፖርት 22,600km2 ርጥበታማ ቦታ ነበራት። የአገሪቱን 2 በመቶ የቆዳ ስፋት የሚሸፍን። ነገርግን ያሉበት ሁኔታና የአደጋ ተጋላጭነት በውል አልተሰነደም። በስምጥ ሸለቆና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል 43 ቦታዮች ተሰንደዋል። ጣናን ጨምሮ የሰሜኑ ይዞታዎች አልተካተቱም። ይህ ባለመሠራቱም ከ 1983 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 52 በመቶው የርጥበታማ ቦታዎች ይዞታ ወደ ደረቅ መሬትና የርሻ ቦታነት ተለውጧል።

በጣና ጉዳይ ከዚህ በፊት ባቀረብኩት ፅሁፍ ላይ በ UNESCO ምክትል ዋ.ዳይሬክተርና የቻድ ሀይቅን ለመታደግ 60 ቢሊዮን ዶላር ከአለማቀፉ ማህበረሰብ ፈንድ ሲሰበሰብ ባለድርሻ የነበሩት ኢትዮጵያዊ Getachew Engida ሀሳባቸውን እንዲጠቁም ጠይቄያቸውም ነበር። እሳቸው በአጭሩ “የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው ዋናው የመፍትሄ ቁልፍ፤ በበኩሌ አገሬን ለመርዳት ዝገሸጁ ነኝ…” ነበር ያሉት።

የኬኒያ ተሞክሮ የሚያሳየንም ይህንኑ ነው። አገሪቱ ከ RAMSAR CONVENTION ጋር የተጣጣመ ህግ አፀደቀች። 6 ሳይቶችን አስመዘገበች። ከ 120 ሺህ ሄክታር በላይ ርጥበታማና የውሃ ሀብቷንም በአለማቀፍ ፈንድ እየተንከባከበች ትገኛለች። ተጨማሪ ሳይቶችን ለማስመዝገብም እንቅስቃሴ ላይ ነች።

ጣናም ሆነ ሌሎች 43 የውሃ አካላት ዙሪያ ያሉን ርጥበታማ ቦታዎች የራምሳር መመዘኛን የሚያሟሉ ናቸው። በተለይም ጣናን ramsar ካስቀመጣቸው መስፈርቶቹ አኳያ እንደሚከተለው እንመልከት።

  1. አደጋ የተደቀነባቸውን ዝርያዎች የያዘ ከሆነ
    ጣና 3672 .ኪ.ሜ ስኩዌር ስፋት ነበረው። አሁን ወደ 3000 ወርዷል። ማለትም የሐዋሳና የዘዋይ ሐይቆች ተደምረው የሚያክል የሃይቁ ክፍል ወደ የብስነት ተቀይሯል።
  2. አደጋ የተደቀነባቸው የእንስሳትና ዕፀዋት ዝርያዎች ያሉበት ከሆነ፣ …የጣና ርጥበታማ ቦታ የሀይቁን 2.1 በመቶ ይሆናል። ከ 2 አመት በፊት በወጣው ሪፖርት መሠረት የሀይቁ 24 ሺ ሄክታር የውሀ ክፍል በእምቦጭ አረም ተወሯል።
  3. ከ 20 ሺህ በላይ አዕዋፋትን የያዘ ከሆነ፣

…ጣና 217 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች ወደ ሀያ ሺ በሚደርስ አሀዝ በሀይቁ ዙሪያ ይገኛሉ፡፡

  1. የቸኛ ዓሳ ዝርርያ፣ ንዑስ ብቸኛ የዓሳ ዝርያ… መገኛ ከሆነ

…ጣና ከ 67 በላይ የአሳ ዝርያዎች (ከግማሽ በመቶ በላይ በሀገር ውስጥ ብቻ የሚገኙ)፡፡….
…………………..

የጣና wetland ቦታዎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። ጉና፣ ግሽ አባይ፣ ፎገራ፣ ጮቄ፣ ደምቢያ፣ ርብ፣ መገጭ ከመገኛዎች ውስጥ ዋናዎቹ ሲሆኑ ባጠቃላይም በ 3 ዞኖችና 29 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

በመጨረሻም፣ ጣናን ለመታደግ ውጤታማው ተግባር የህግ ማዕቀፍ ነው። በዚህም ከ ramsar convention ጋር የተጣጣመ ህግ ማፅደቅ። ይህን ለማድረግም አቶGetachew Engida ን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዲሁም በአሜሪካና አውሮፓ ያሉ ስለ ጣና እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ዜጎችን ማሳተፍ ተገቢ ነው።

መንግስት ይህን ህግ ያፀድቅ ዘንድ ጥሪያችንን እናሠማ!❤


References

Abunie, L. (2003). The distribution and status of Ethiopian wetlands: An overview. In: Abebe, Y., and Geheb, K. (eds.).Proceedings of a seminar on the resources and status of Ethiopia’s wetlands. pp. 116.Ajibola, M.O., Adewale, B.A., and Ijasan, K.C. (2012).Effects of urbanization on Lagos wetlands. International Journal of Business and Social Science.3: 17.ANRSBA (Amhara National Regional


Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories