ኢትዮጵያ፡ የአፍሪካ ቀንድ ጥልፍልፍ ከሰሞኑ

…የእንግሊዙ ኩባንያ የጀመረውን ነዳጅ ቁፋሮ ሕገ-ወጥ ስትል ሞቃዲሾ አስጠንቅቃለች

የዓባይ፡ልጅ ✍️

የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ የአፍሪቃ ቀንድ ስምሪቱ የትኞቹ ቅድመ-ነገሮችን እየተከተለ እንደመጣ ማውሳት አንድምታውንም የመመልከቻ አንዱ መስታውት ሊሆን ይችላል። በቀድሞው የሶማሊያ መሪ ፋርማጆ ላይ የተደረጉ ቅንጅታዊ ፕሮፓጋንዳዎች፣ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንሰጥሻለን የሚለው ተስፋ እና እነሱንም ተከትለው የተከሰቱ ለውጦች ለአሁኑ የቀንዱ ትዕይንት መንደርደሪያዎች ነበሩ።
በሶማሊያው ሀገራዊ ምርጫ ፋርማጆን አሸንፈው ወደ ቪላ ሶማሊያ ለተመለሱት ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ ከምዕራባዊያኑ የታዘብነው ነገር “አሻንጉሊታችን አሸነፈልን” አይነት ነበር። ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድም በቪላ ሶማሊያ ስራቸውን ጀመሩ። በርግጥም የሞቃዲሾ-ዋሽንግተን ቅርርብ መሻሻል ለማሳየት አልተቸገረም። በዚህ ረገድ ዝርዝር ትብብሮችንና ያልተሰሙ እውነታዎችን ሳንጨምር፣ ቁልፍ በሚባሉ የዋሽንግተን አጀንዳዎች ላይ ሐሰን ሼክ በራሳቸው የወሰኑትን ሲያከናውኑ ተመልክተናቸዋል። ከአስመራ ጋር በሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ እንዲሁም ሞቃዲሾ ከቤይጂንግ ግንኙነቷ ላይ ያሳየችው አቋም ለምዕራባዊ ጉልበተኞች አስደሳች አልነበረም። ፕሬዝደንት ባይደን በይደር ያስቀመጡትን የሶማሊላንድ ካርታ እዚጋ ነው የመዘዙት…።
በፈረንጆቹ ታህሳስ 18 የአሜሪካ ወታደራዊ መጓጓዣ አይሮፕላኖች ከጂቡቲው ቤዝ የጫኗቸውን የጦር ባለስልጣናት በርበራ ወደብ የማድረሳቸውና፤ በዚያም ከሀርጌሳ አቻዎቻቸው ስለ ወታደራዊ ትብብር መምከራቸው በስፋት ተዘገበ። [1] በተጠቀሰው ወር ከታህሳስ 4 እስከ 14 ባሉት ቀናት ውስጥ የአሜሪካ ወታደራዊ ካርጎዎችና መጓጓዣዎች ምልልስ ስለማብዛታቸው ከበረራ አሳሽ ዌብሳይቶችም ማስረገጥ የምንችለው ነው። [2]
ከነዚህ ቀናት በኋላ እንግሊዝ በሶማሊላንድ እና ሶማሊያ አወዛጋቢ መሬቶች ላይ የነዳጅ ማውጣት እንቅስቃሴ ጀመረች። Genel Energy የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአወዛጋቢው መሬት የጀመረው የነዳጅ ማውጣት ጅማሮ ከቪላ ሶማሊያ የገጠመው ያልተጠበቀ የሚባል ነበር። ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ እንግሊዝ ድርጊቱን እንድታቆም ነበር ይፋ ያደረገው ዲሴምበር 29 ላይ..። [7] ይህ ማስጠንቀቂያ በተሰጠ ማግስት ነበር በሶማሊያ-ሶማሊላንድ አወዛጋቢ ከተሞች ንፁሃንን መግደልና ማፈናቀል የተጀመረው።

ይህ ጥቃት የደረሰው አሜሪካ ባስታጠቀችው አማፂ ኃይል መሆኑ በሂደት የተገለፀ ሲሆን በሮይተርስ የትላንት በስቲያ ዘገባ ደግሞ “በሶማሊያ ራስ-ገዝ አካባቢዎች በመንግስት ተቃዋሚዎችና በጸጥታ ሃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት በትንሹ 20 ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱም ከሳምንት በላይ ሆኖታል።” የሚል ነበር። [3]

ያልታጠቁ ዜጎች አሜሪካ የምትደግፈው በተባለው ታጣቂ ቡድን የተገደሉት በስተ-ምሥራቅ በሶማሌላንድ እና በአጎራባች ፑንትላንድ መካከል የምትገኘው አወዛጋቢ ከተማ የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ ይዞታዎች አንዷ ናት።
ግድያው ሲካሄድ “ሶማሊላንድ ከተማዋን ለፑንትላንድ መስጠት አለባት የሚሉ ተቃዋሚ ዜጎች የሞቃዲሾ መሪዎቻቸው ከጥቃት እንዲጠብቋቸውም ሲጠይቁ ነበር ተብሏል።

የብሪታኒያው ጄነል-ኢነርጂ የጀመረውን “ህገ-ወጥ የነዳጅ ቁፋሮ ውድቅ ያደረገው የሐሰን ሼኽ መንግስት የነዳጅ ሚኒስቴር በመግለጫው “በሶማሊያ ግዛት ፍቃድ የመስጠት ብቸኛው ሕጋዊ መስሪያ ቤት እኔ ብቻ ነኝ።” ያለ ሲሆን “የትኛውም ሀገር ቢሆን የሶማሊያን ሉዓላዊነት የመጣስ መብት የለውም” ሲል ተደምጧል።
ሶማሌላንድ እንደ ሀገር ዓለም አቀፍ እውቅና ባይኖራትም በፈረንጆች 2020 ግን የእንግሊዝ፣ የዴንማርክ እና የኔዘርላንድ መንግስታት የሶማሌላንድን የኢኮኖሚ እድገት ይደግፋሉ የተባሉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን የማልማት 4 ስምምነቶችን ማፅደቃቸው የሚታወቅ ነው። ይህም የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚፃረር ሲሆን፤ ቪላ ሶማሊያ ለእንግሊዝ የሰጠችው ማስጠንቀቂያ ደግሞ የሐሰን ሼክ አሁናዊ አሰላለፍ ከነማን ጋር ሊሆን እንደሚችል የሚያመላክት ነው። ይህ ተቃርኖ በአዋሳኝ የሀገሪቱ ግዛት የዜጎች ግድያና ማፈናቀልን ሲያስከትል ገዳዩ ቡድን ደግሞ በአሜሪካዊው ሴናተር ይፋዊ ድጋፍ የተደረገለት ቡድን መሆኑ ነው በአሜሪካ የሚገኙ የዜና አውታሮች ያጋለጡት።[4]

ከዘጠኝ ወር በፊት መጋቢት 18፣ 2022 ላይ መቀመጫው በአሜሪካ ኢዳሆ የሆነው ኢዳሆ ትሪቡን “የኢዳሆ ሴናተር ጂም ሪሽ ሶማሊያ ውስጥ ለተገንጣይ አማፂያን ጋር ያደረጉት አዲስ “የደህንነት ትብብር” ግጭት እያስከተለ እንደሆነና ወደ የእርስ በርስ ጦርነት ሊያመራም እንደሚችል አስጠንቅቋል። [5]

አሁን፣ ልክ ከ 9 ወራት በኋላም፣ የሶማሊያ ብሄራዊ ንቅናቄ (SNM) ጋር ግንኙነት ያላቸው ተገንጣይ ሃይሎች ከዩናይትድ ስቴትስ (የደህንነት አጋራቸው) ያገኙትን ስልጠናና የጦር መሳሪያ ተጠቅመው በላሶን ሲቪሎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል።” ኢዳሆ ትሪቡን አስነብቧል። ይህ የዜና ምንጭ አክሎም “አሁን ላይ ከፍተኛ መፈናቀል እየተካሄደ ነው። የመገናኛ ዘዲዎችም ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል። ካቱቶ የሚባለው በነዳጅ የበለፀገ አካባቢ የሶማሊያ ህጋዊ የፌዴራል መንግስት አካል መሆን ቢፈልግም ምስጋና ለአሜሪካዊው ሴናተር ጂም ሪሽ ይግባውና የላስቲን ጎዳናዎች በንፁሃን ዜጎች ደም ተጠለቅሎቋል።” ሲል የዘገበው።

ሴናተር ሪሽ ከሶማሊያ ግጭት ባለፈ በዩክሬን የአሜሪካ የተልዕኮ ጦርነት ግንባር ሲሆኑ ከባልደረቦቹ ሪፐብሊካኖች በሁለቱም ዙር ከ 50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወደ ዩክሬይን የዘለንስኪ አገዛዝ እንዲላክ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ርምጃለውን የተቃወሙ ሰዎችንም ሁሉ “የፑቲን ደጋፊዎች” በማለት መወረፋቸውም ተነግሯል።
ብሪታኒያ በሶማሊላንድ የጀመረችውን ጣልቃ ገብነትና ነዳጅ ፍለጋ ተከትሎ የተቀሰቀው ግድያና አመፅ በተቀሰቀ በቀናት ውስጥ ነው የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ በቀንድ ሀገራት ለመሰማራት ጉዞ የጀመረው።

ይህ በንዲህ እንዳለ፤ የእንግሊዙ አምባሳደር ከትግራይ ጦርነት ወዲህ ገለልተኛ ነኝ የሚል መግለጫ መስጠቱን የሰማነው። በዛሬው ዕለት የምዕራባዊያን ልሳን በመሆኗ በበርካቶች የምትወገዘው አዲስ ስታንዳርድ በኢትዮጵያ የእንግሊዙ አምባሳደር “ትኩረታችን በጦርነቱ የተጎዱ ንፁሃንን ማዳን እንጂ በአንድ ወገን በኩል ጫና መፍጠር አልነበረም።” ብለዋል ስትል አስነብባለች።[15]

አሜሪካ የብሔራዊ ዘብ ተጨማሪ ወታደሮቿን በአፍሪቃ ቀንድ ማሰማራቷ ምን ይፈጥራል የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ሲሆን ቀደም ያሉ አርቲክሎቼ ላይ ምላሽ እንደሚገኝ አምናለሁኝ።[6]
የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ፣ የአሜሪካ መደበኛ ሰራዊት፣ የግል ወታደራዊ ተቋራጮች ወዘተ አልሸባብን፤ ቦኮ ሐራምን፤ ISISን እና ሌሎችም ራሷ አሸባሪ የምትላቸው ቡድኖችን [8] በሌላ ጎራ ደሞ የመሳሪያ፣ የስልጠና እና የመሳሪ ድጋፍ በማቅረብ ስትራቴጂክና ማዕድን ያለባቸው ቀጠናዎችን በግጭት አስገብታ ብዝበዛ ታካሂዳለች የሚለው በስፋት የተነገረው እውነታ ነው።[6]
የአሜሪካ ጦር በርበራ ላይ በተለይም ከታህሳስ 14 እንቅስቃሴዎቹ ወዲህ ብቻ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አይሮፕላኖች በቀጣናው ሀገራት ሲመላለሱ ተስውለዋል።[9] በዋነኛነትም የግብፁ ወደ ፖርት ሱዳን [8] የቱርኩ ወደ ሶማሊያ [12] የሩሲያው የ Emergency Monitor ግዙፍ አይሮፕላን ወደ ጂቡቲ [11] እንደገና የግብፁ ወደ ፖርት ሱዳን [12] የኢማራት ወደ ካርቱም [13] የእስራኤሉ ወደ አዲስ አበባ በመቀጠል ወደ ኮንጎ [18] ወዘተ የአፍሪካ ቀንድን በወታደራዊ ስለላና ቅኝት ሲዞሩት ሰንብተዋል።
ምስራቅ አፍሪካ የቻይና፣ የሩሲያና የሌሎችም ሀገራት ስትራቴጂክ ቀጣና ብሎም የወታደሮቻቸው መገኛ በመሆኑ የአሜሪካ አካሄድ ከተቀሩት ኃያላን ባላንጣዎቹ ግጭት ፈጥሮ የቀንዱን ቀጣና “እንኳንም ዘንቦብሽ” እንዳስብለው በብርቱ ተሰግቷል።

የዓባይልጅ ✍️ Esleman Abay

#HornOfAfrica #Somalia #Somaliland #AlShabaab #NATO #PENTAGON

➖ዋቢዎች

  1. የሶማሊላንድ አሜሪካ ወታደራዊ ትብብር
    https://somalilandchronicle.com/2022/12/18/security-cooperation-between-somaliland-and-united-states-gets-underway/
  2. American backed forces kill civillians in Somalia:
    https://www.idahotribune.org/news/over-20-dead-in-somalia-after-us-backed-fighters-open-fire-on-civilians-idaho-senator-rischs-security-partnership-stokes-conflict
  3. Reuters, 20 dead in Somaliland:
    https://www.reuters.com/world/africa/least-20-people-killed-clashes-somaliland-2023-01-01/
  4. Senator will cause war..
    https://www.idahotribune.org/news/idaho-senator-pushing-to-ukraine-somalia-with-secessionist-government-bill-could-spark-civil-war-in-the-country-causing-potential-mass-migration-to-idaho
  5. US Senator agreement to separatist Somaliland forces:
    https://www.idahotribune.org/news/idaho-senator-pushing-to-ukraine-somalia-with-secessionist-government-bill-could-spark-civil-war-in-the-country-causing-potential-mass-migration-to-idaho
  6. ፔንታጎን የአሸባሪዎች ማህፀን፡
    https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2667978529999670&id=100003626461788&mibextid=Nif5oz
  7. Hassan sheik warn UK to respect somalia’s sovereignty
    https://www.arabnews.com/node/2223706/business-economy
  8. Egypt to mogadishu, Djibouti

  1. Us – 3rd mission in a row for the same USAF C130J (07-1468) fm #Djibouti heading to #Berbera #Somaliland. Something special seems to happen
    https://twitter.com/Laurent_Le_Bloa/status/1603014568464486404?t=ubgcqB_SjsGy4U3pbNygew&s=19
  2. US – USAF C130 #ROGUE52 returned to #Djibouti and conducted immediatly a second mission to #Berbera #Somaliland
    https://twitter.com/Laurent_Le_Bloa/status/1602989619099885569?t=9ruN-iXsmA6q71lASOQWMQ&s=19
  3. Russia to Djibouti:
  1. Egypt to Port Sudan – Landing 11h00 local time, return less 1 hour later https://twitter.com/Laurent_Le_Bloa/status/1604804769213829124?t=PE5GJoUobcwKsAnyoi67rQ&s=19
  1. UAE to Kartoom :
    https://twitter.com/Laurent_Le_Bloa/status/1605157442102661121?t=O1_tka6Laa-eMIEKzNANpA&s=19
  2. Morocco to Djibouti :
  1. የእንግሊዝ አምባሳደር በኢትዮጵያ
    https://amharic.addisstandard.com/%e1%89%83%e1%88%88-%e1%88%9d%e1%88%8d%e1%88%8d%e1%88%b5%e1%8d%a1-%e1%8b%8b%e1%8a%90%e1%8a%9b-%e1%89%b5%e1%8a%a9%e1%88%a8%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8c%a6%e1%88%ad%e1%8a%90/
  2. ሰላም አስከባሪ ወደ ወልቃይት?
    https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2611440075653516&id=100003626461788
  3. በወልቃይት ልቡ የወለቀው አውሮፓ
    https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2731592556971600&id=100003626461788&mibextid=Nif5oz
  4. Israel H800XP 4X-CUZ fm #TelAviv probably to #AdisAbaba #Ethiopia
    landing unnoticed https://twitter.com/Laurent_Le_Bloa/status/1609585181756690433?t=Cynn_UJYjmH_BTnAq90JCA&s=19

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories