የዓለማችን የመጀሪያው ዩኒቨርሲቲ እና ባሻገር

ዩኒቨርሲቲው የተቋቋመው በእንስት–በአፍሪካዊት መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል።
ዩኒቨርሲቲው በሞሮኮ ነው የሚገኘው። አል-ቃራዊን ዩኒቨርሲቲ ይሠኛል። በ 859 AD የተመሠረተው በወጣቷ ልዕልት ፋጢማ አል-ፊኺሪ ነበር። UNESCO እና Genius world Records ይህንኑ መዝግበዋል።
መሥራቿ ፋጢማ በአሁኗ ቱኒዚያ ያኔ ቃራዊን በሚባል ከተማ ታዋቂና ሐብታም ነጋዴ የነበረው ሙሐመድ አል-ፊኺሪ ልጅ ናት። ከ 1200 ዓመታት በፊት ወደ ሞሮኮ ያቀናው አባቷ ከሞተ በኋላ ያላቸውን ሐብት ይህ ተቋም ይመሠረት ዘንድ የፋጢማ ችሮታ ሆነ።
በመጀመሪያ መስጂድና የእስልምና አለማቀፍ የትምህርት ማዕከል ሆኖ ነበር የጀመረው። 22 ሺህ ምዕመናንን የሚያስተናግዱ ክፍሎችም ነበሩት።
በመቀጠል ደግሞ የሕክምና፣ ፅሕፈት፣ አስትሮኖሚ፣ የአረብኛ ሰዋስው፣ ሙዚቃና ሌሎችንም ማስተማር ጀመረ። በሂደትም ኬሚስትሪ፣ የውጭ ቋንቋና ፊዚክስ ማሰልጠን ቀጠለ። በ 1947 እኤአ በሞሮኮ መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ውስጥ ተመዘገበ። ከዛም “University of al- Qarawiyyin” ተብሎ ለበርካታ ሺህ የአገር ውስጥና አለማቀፍ ሰልጣኞች የስኮላርሺፕና ምርምር እድልን በስፋት እያቀረበ ይገኛል።

የዓለማችን ግምባር ቀደም ቤተ መፃህፍትም ከ 4,000 ሺህ በላይ ኦሪጂናል ጥራዘ ድርሳናትና ሌሎችንም ይዞ በዚሁ በአል-ቃራዊን ዩኒቨርሲቲ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይገኛል። Al Jazeera 2016 ላይ ስለ ቤተ መፅሐፉ ያነጋገረው አብዱልፈታህ የተባለ የቤተ መፅሐፉ ባለሙያ “..ከዓለም ዙሪያ ሠዎች ወደ እኔ ይመጣሉ። ምክንያት ደግሞ የመረጃዎችን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ በዚህ የሚገኙ ጥንታዊና ኦሪጂናል ድርሳናትን ስለሚያገኙ…” ነበር ያለው።

BBC በ Travel ፕሮግራሙ የዛሬ ሁለት አመት በሞሮኮ አል-ቃራዊን ዩኒቨርሲቲን አስቃኝቶ ነበር። በዚህም፣ በዩኒቨርሲቲው በሚገኙ ሊቃውንትና ጥንታዊ ድርሳናት ሠልጥነው ህያው አሻራቸውን ለዓለም ያበረከቱ ጉምቱ ልሂቃን ውስጥ የተወሰኑትን ጠቃቅሷል።
pope sylvestre II, በዚህ ዩኒቨርሲቲ በመሠልጠኑ በ 10ኛው መ.ክ.ዘመን ወደ አውሮፓ ሲመለስ የአረብኛ ቁጥሮችን ለአውሮፓውያን ያስተዋወቀ ሆኗል። “Relation between Islam and philosophy” እና በሌሎችም የራሱ ወጥ እሳቤዎች አለም “የእስልምናው ፈላስፋ” ሲል የሚጠራው ኢብን ሩሹድ በዚሁ ተቋም ነበር የተማረው፣ የተመራመረው። ኢብን ሩሹድ ከ 100 በላይ መፅሐፍትን የከተበ፣ የአል-ሞሐድ ስርወ መንግስት ጠቅላይ አቃቤ የነበረ፣ የአርስቶትልን እሳቤ ኮመንተሪ በስፋት ያቀረበባቸው 3 የፍልስፍና መፃህፍት የፃፈ፤ በተጨማሪም በስነ መለኮት፣ ሒሳብ፣ ስነ-ከዋክብት፣ ፊዚክስ፣ ሕክምና፣ ሕግ፣ ስነ-ልሳን ወዘተ…የታወቀ ነው። በህክምና ዙሪያ የፃፈው ስራው በላቲን ተተርጉም ለበርካታ ክፍለ ዘመናት በአውሮፓ መማሪያ መፅሐፍ ሆኖ አገልግሏል።
በዚሁ በአል-ቃራዊን ከሠለጠነ በኋላ….

በኢራቅ ሞሱል እና በሌሎች አገራት በርካታ የአረቡ አለም ጥንታዊ ድርሳናት በሽብርና ጦርነት ወድመዋል። አል-ቃራዊን ቤተ መፃህፍት በአንፃሩ በመንግስት ልዩ ትኩረት በቴክኖሎጂም የታገዘ የመረጃ ሥነዳ ጀምሯል። ከሁሉም በላይ ይላል Daily Sabah, በዘጠነኛው መ.ክ.ዘመን በቆዳ ላይ የተከተበው ኦሪጂናል ቅዱስ ቁርዓን በቤተ መፅሐፉ በልዩ ጥበቃና አያያዝ ላይ ይገኛል።

ፋጡማ የመሠረተችው ዩኒቨርሲቲ ለዛሬዋ ዓለማችን የሚጨበጥ ብርሐን ማበርከቱን ዛሬም እንደቀጠለ ይገኛል።

እናመሠግንሻለን ወጣቷ የዕውቀት ልዕልት ፋጢማ |

አፍሪካ የሰብዓዊ ፀጋዎች መነሻ ?

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories