
By Esleman Abay – የዓባይ:ልጅ እስሌማን ዓባይ
በዘንድሮው የውሃ ሙሌት ላይ የግድቡ የመሀከለኛ ኮሪደር ከሚገኝበት የ 625 ሜትር ከፍታ ጋር ሲሰላ 25 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ ግድ የሚል ነው።
በመስከረም ወር የዓባይ ወንዝ የሚያቀርበው የውሃ መጠን በአማካኝ 19 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያህል ነው።
በሌላ በኩል ቀደም ባሉት ሙሌቶች ወቅት የግብፅ ታላቁ የአስዋን ግድብ እስከ 182 ሜትር ድረስ ሞልቶ ወደ በረሃዎችና ወደ ሜዲትራኒያን ባህር መፍሰስ የጀመረው ነሐሴ ላይ ጀምሮ ነበር። በዚህም 40 BCM እና ከዚያም የበለጠ ውሃ ወደ ሜዲትራኒያንና ወደ ምድረ በዳ ቦታዎች ለመፍሰስ መገደዱን የራሳቸው የግብፅ የዘርፉ ፕሮፌሰር ሐፌዝ በሳቴላይት መረጃዎች ማስረገጣቸው የሚታወስ ነው። (መረጃው ያስፈለገው ቢኖር የማጋራው ይሆናል።)
ታዲያ የዘንድሮው ጫን ያለ ክረምት ካለፉት አመታት የበለጠ ውሃ ተርፎ ወደ ሜዲትራኒያን እንደሚፈስ እየተመላከተ ባለበት የግድቡ ሙሌት ሐምሌ እና ነሐሴን ዘልሎ ወደ መስከረም ለማዘግየት የታሰበው ለምን ይሆን?
25 BCM ውሃ መያዝ በሚጠይቀን የሙሌት ወቅት የስድስት ቢሊይን BCM ጉድለት ወደሚያስከትለው ወደ መስከረም ወር ለመግፋት ምንም ምክንያት በሌለበት ግዴታ ያመጣብን መንስኤ ካለ [እሱን] ለህዝብ ማሳወቅ ያልተፈለገው ለምን ይሆን? ..
ምክንያት-አልባው የዘንድሮው ሙሌት በግብፅ ስራ ይጀምራል ለተባለው (ኢትዮጵያ ላተልማከረችበት) ሰው ሰራሽ ወንዝ (artificial river) ቅድሚያ የሰጠ ይሆን? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱም አይቀርም።
በአቡ ዳቢ የሚደረገው ድርድር ከግብፃዊያን ሚዲያዎች አልፎ በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳይቀር ይፋ መደረግ የጀመረ እውነታ ሆኗል። ታዲያ የአቡ ዳቢው ድርድር እንዲህ ምክንያት የሌለው የሙሌት መርሃ ግብርን ሊወልድ የሚችል ነውን? እነዚህን ጥያቄዎች አለመመለስ ብቻ ሳይሆን አለመጠየቅም ታሪካዊ ስህተት ይመስለኛል።
በዋሽንግተኑ ለጥቂት የተረፍንበት ‘ፋውል’ በአቡ ዳቢ እንዳይደገም የሚለው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ምኞት ነው።
#ዓባይ #gerd4thfilling #GERD #Ethiopia #African_DAM #የዓባይልጅ #eslemanabay
- Medvedev suggests organizing permanent forum to oppose neocolonialism
- Fertility intention among married women in Ethiopia: a multilevel analysis of Ethiopian demographic health survey 2016
- 5 Quotes From French Leaders That Reveal How Much France Depends on Africa for Its Survival
- It’s time to eliminate unnecessary military spending
