Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the matomo domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-includes/functions.php on line 6131
የሳዑዲው አል-አረቢያ ያስነበበው የዓባይ ውኃ ጉድ - የዓባይ ፡ ልጅ
Deprecated: Creation of dynamic property OMAPI_Elementor_Widget::$base is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/optinmonster/OMAPI/Elementor/Widget.php on line 41

የሳዑዲው አል-አረቢያ ያስነበበው የዓባይ ውኃ ጉድ

የዓባይ:ልጅ Esleman Abay

...ከዓባይ አመታዊ ፍሰት 20 ቢሊዮን ኪዩቢክ ድርሻ ለማግኘት ኢትዮጵያ ያቀረበችው ፕሮፖዛል በካይሮ ውድቅ ተደርጓል...

የህዳሴ ግድቡን ቴክኒካል ጉዳዮች በዝርዝር ጠንቅቀው የሚያውቁ የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር ምንጭ ነግረውኛል ያለው የሳዑዲ አረቢያው አል አራቢ አል-ጃዲድ “ከኢትዮጵያ በኩል የአቋም ድርቅናው እንደቀጠለ ነው፤ ለመስማማት ቅን ልቦናም አለመኖሩ ተስተውሏል።” ሲል አስነብቧል።

“በአስገዳጅ ስምምነት እንዲፈረም ካይሮ የፀና አቋሟ የሚቀጥል ነው” በማለት የግብፁ የመረጃ ምንጭ ነግሮኛል ያለው Al-Arabia ፣ ካይሮ ከድርድሩ የምትሻው አጀንዳ ”የህዳሴ ግድቡ ጉዳይ አይደለም፤ ምክንያቱም ህዳሴ ግድቡ በአንድ ወገን ተገንብቶ እየተጠናቀቀ Fait Accomplai’ ሆኗልና፤ ይሁንና በህግ ካልታሰረች ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌላ የግድብ ፕሮጀክት ይፋ ስታደርግ የግብፅ ዋነኛው ቀውስ አሀዱ ብሎ ይጀምራል።” ብለዋል።

“ግብፅ የኢትዮጵያን እቅድ አለመቀበሏን አሳውቃለች” ያለው የአል-አረቢ ዘገባ፣ “ከዓባይ/ናይል ወንዝ አመታዊ ፍሰት 20 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ድርሻ ለማግኘት ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ፕሮፖዛል ውድቅ አድርጋዋለች።” ሲሉ ነግረውኛል ብሏል።
በዚህ ጉዳይ በቀደሙት የድርድር ዙሮች ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከኤምሬትስ የተሳተፉት ታዛቢዎች በተገኙበት ድርድር ላይ በይፋ የታዘቡት ነው።” በማለትም አልአረቢ ፅፏል።
አልአረቢ አክሎ በዘገበው የካይሮው ሰው መረጃው “የናይል/ዓባይ ተፋሰስ 3.4 ትሪሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያለው ሲሆን ኢትዮጵያ የ 150 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ድርሻ ሲኖራት፣ ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር፣ ግብፅ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ድርሻ ነው ያላቸው።” ሲል አስነብቧል።

ይህ የሳዑዲ አረቢያ ሚዲያ (አልአረቢያ) ምን አይነት ጉድ ነው የሚያስደምጠን!?

የዓባይ ልጅ Esleman Abay

Share:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

VK Russian online social media and social networking service
Categories