Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the matomo domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-includes/functions.php on line 6131
“የኃያላኑ ስትራቴጂክ ፍርሃት – የአፍሪካ አንድነት! - የዓባይ ፡ ልጅ
Deprecated: Creation of dynamic property OMAPI_Elementor_Widget::$base is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/optinmonster/OMAPI/Elementor/Widget.php on line 41

“የኃያላኑ ስትራቴጂክ ፍርሃት – የአፍሪካ አንድነት!

በማዕድን ሐብት ከየትኛውም አህጉር የማይወደር ፀጋ የተለገሳት አህጉረ-አፍሪካ ከ 90 በመቶ በላይ የአለምን የፕላቲኒየም ማዕድን፣ 50 በመቶው የወርቅ ማዕድን፣ 50 በመቶው የአልማዝ ሐብት እና 33 በመቶ የዩራኒየም ማዕድን ባለቤት ናት – ይህ ግዙፍ ሐብቷ እስካሁን ያመጣላት ትርፍ የልጆቿን ሰቆቃና በዝባዦቿን ከማደለብ ባይሻገርም።

ባለ ጠጋዋ አፍሪካችን፣ የዓለማችንን 60 በመቶ ያልታነካ ለም መሬት ይዛ ተቀምጋለች። ተፈጥሮ ከለገሰቻት 874 ሚሊዮን ሄክታር ለም መሬቷ 179 ሚሊዮን ሄክታሩን ብቻ ነው የምታርሰው፤ እሱም ምርታማነቱ ባልተሻሻለ ዘዴ የሚከናወን በመሆኑ ራሷን መመገብ አላስቻላትም።

በአንፃሩ በአፍሪካ እየታረሰ ከሚገኘው የመሬት ስፋት ሩብ እንኳን የማይሞላ መሬትን በውጤታማ ዘዴ ያረሰችው ዩክሬይን ለአፍሪካ ስንዴ አቅራቢ መሆኗ እስከ ቅርብ አመታት የተመዘገበ እውነታ ሆኗል።
በዚህ የተነሳም አህጉራችን ከአመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ 1/3ኛውን ከሩሲያ፣ 12 በመቶውን ደግሞ ከዩክሬይን የገለፀው ተመድ (UNCTAD) በቅርብ ባወጣው ሪፖርቱ ሲሆን አሀዞቹ በተለይም እስከ 2020 በነበሩት ሁለት አመታት መመዝገባቸውን ይጠቅሳል።

ተከታዩ የድህረ ቅኚ ገዢዎች ዘላቂ መርሆ ነው… “Who controls the food supply controls the people; who controls the energy can control whole continents; who controls money can control the world.”

የአፍሪካ ተመፅዋችነትና ድህነት ለምዕራባዊ ሀገሮች የሀብት መሠረትና የፈጣን ዕድገታቸው ምሰሶ መሆኑን የገለፁት ጎምቱ፣ አንድሬ ጉንደር “በዓለም ዙሪያ ያሉ ደሃ ሀገራት በተለይም የሰሃራ በታችና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ናቸው።” ብለውናል። ለዚህም ነው አፍሪካን ለሃምሳ በጣጥሰው እምቅ ጉልበቷ በተቃርኖ ፍትጊያዎች እየመከነ ለግልቢያ የተመቸች አህጉር ያደረጓት።

የአፍሪካ አንድነትና የልጆቿ መተባበር የኃያላኑ ስትራቴጂክ ስጋት ነው!

እስሌማን ዓባይ #የዓባይልጅ #eslemanabay

Share:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

VK Russian online social media and social networking service
Categories