Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the matomo domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-includes/functions.php on line 6131
የአየር ንብረት ለውጥ የወቅቱ ፓን-አፍሪካዊ አጀንዳ - የዓባይ ፡ ልጅ
Deprecated: Creation of dynamic property OMAPI_Elementor_Widget::$base is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/optinmonster/OMAPI/Elementor/Widget.php on line 41

የአየር ንብረት ለውጥ የወቅቱ ፓን-አፍሪካዊ አጀንዳ

ኢትዮጵያ የአፍሪካን ድምፅን ለአለም ማስደመጥ ታሪኳን የሚመጥን ርምጃ ነው። አሁን ላይ በአየር ንብረትና ታዳሽ ሃይል ዙሪያ አፍሪካዊ ምሁራን የሚያሰሙትን ድምፅ አገራችን ብትመራው ይጠቅማል የሚል እምነት አለኝ።

ምዕራባዊያን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል በሚለው ዘመቻቸው ወደ ታዳሽ ኃይል ሽግግር እንዲደረግ በሰፊው እየሰሩ ናቸው። ለዚህም አህጉረ አፍሪካ በፈረንጆቹ 2050 ሙሉ ለሙሉ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ትሆን ዘንድ ስምምነቶች እየተደረጉ ናቸው። ይህንኑ ለማሳካትም ያደጉ አገራት ለአፍሪካ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ፋይናንስ እናደርጋለን ብለዋል። ከዚህ ባሻገርም ደግሞ ታላላቅ ኩባኝያዎቻቸው አረንጓዴውን የኢኮኖሚ አካሄድ የማይከተሉ ዘርፎች ላይ ገንዘብ ማፍሰስና ድጋፍ መስጠት እንዲቀንሱ ብሎም እንዲናቆሙ መደረግ ጀምሯል። ይሁንና ይህ አካሄድ ለአፍሪካ አደገኛ ነው ተብሏል። ልብ በሉ አረንጓዴ ሽግግሩ አይደለም የተተቸው Just Transition እየተባለ የሚገኘው አፍሪካን ካደጉ አገራት ጋር ተሸጋገሩ የሚለው ዘመቻ ነው።

‘Just Transition’ እየተባለ የሚገኘው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር ርምጃ በዋናነት የነዳጅ ዘይትና ተፈጥሮ ጋዝ ክልከላ ዋነኛ አካሄዱ በመሆኑ ለአፍሪካ ‘Bad Transition ነው እየተሰኘ ነው። ዙሪያ ገባውን ያላገናዘበ ሽግግር ነው በማለትም ለአፍሪካ ‘Bad Deal’ ነው እየተባለ ነው።

ነዳጅ ያደጉ አገራት ዋነኛ የእድገት ምሰሶ መሆኑን ምሁራን ይገልፃሉ። አሁንም ቁልፍ የእድገት አቅም ነው። ይሁንና አፍሪካዊያን ነዳጅ ማውጣትና ማግኘት በጀመሩበት በዚህ ወቅት የተጀመረው ርምጃ የአህጉሪቷን የእድገት ተስፋ ያጨልማል የሚል ነው ዋነኛው ስጋት። አካሄዱ ካልተከለሰ አዲሱ የኢኮኖሚ ቅኝ ግዛት መሆኑ አይቀርም እየተባለም ይገኛል።

አፍሪካ በስሯ 125.8 ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ ዘይት የያዘች ናት። ይህም የአለምን 7.7% ማቅረብ የሚያስችላት ነው። ዛሬ ባለው ዋጋ ከ 10.5-ትሪሊዮን ዶላር በላይ ያወጣል። ከአፍሪካ አጠቃላይ አመታዊ ምርት ጋር ሲወዳደርም ከአራት እጥፍ የሚሆን ነው።

አህጉሪቷ 503.3 ትሪሊየን ኪዩቢክ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አላት። ይህም 7.2 በመቶ የአለም ክምችት ድርሻ የሚይዝ ነው። የ30 ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ ይገመታል።
የአለምን 9 በመቶው ፈሳሽ ነዳጅ እያቀረበች የምትገኘው አፍሪካ ናት። ይኸውም 7.2ሚሊዮን በርሜል በቀን በማምረት የሚቀርብ ነው። ከአለምን የተፈጥሮ ጋዝ ምርት አቅርቦት ውስጥም 6 በመቶው ከአፍሪካ የሚገኝ ነው። ይሁንና አፍሪካዊያን ከድህነት በታች እንዳሉ ናቸው።

የአለም ህዝብ 90 በመቶ ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኖ በአፍሪካ ከ 600 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት የማያገኝ ነው። ባለፉት አስር ዓመታት በአለም ከተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ የአፍሪካ ድርሻ 40% ነው። ነገር ግን ከ45% በላይ የሚሆነው ምርት ወደ ውጭ የሚላክ ነው።
አፍሪካ 17 በመቶው የአለም ህዝብ እየኖረባት አለማቀፍ የበካይ ጋዝ ልቀት መጠኗ ግን 2% ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከአለም በካይ አገራት ጋር በእኩል የቤት ስራ ለምን ትጠመዳለች የሚለው አንዱ ስጋት ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ በብክለት ደረጃ አበርክቶ የሌለውን የሃይል አጠቃቀሟን መገደብ ለአህጉሪቷ የማደግ ጅምር አደጋ እየተባለ ነው።
ሲቀጥልም የታዳሽ ሃይል ዘርፉ የስራ እድል ፈጠራው ነዳጅ ከሚጠቀሙ ዘርፎች አንፃር በጣም ያንሳል የሚለውም  ተጠቃሽ ሆኗል።

ለታዳጊ አገራት የታዳሽ ሃይል ሽግግርን ለመደገፍ ከሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ውስጥ ያደጉ አገራት ያወጋጁት ገንዘብ ግን በጣም አነስተኛውን ብቻ መሆኑም ሌላኛው ስጋት ነው።

ይልቁንም ምዕራባዊያኑ በአፍሪካ የታዳሽ ሃይል ላይ በመሰማራት ራሳቸው ከማትረፍ ውጭ ለአፍሪካ ጎጂ ነው የሚሉ ጥናቶችም አሉ። አፍሪካ ስርአት በተበጀለት መንግድም ቢሆን ነዳጇን የግድ መጠቀም አለባት የሚሉ ሙግቶችም ብርታት እያገኙ ይገኛል።

ታዲያ ይህ አፍሪካዊ አጀንዳ በኢትዮጵያ መንግስት የተመራ ይሆን ዘንድ ሀሳብ እሰጣለሁ።

Esleman Abay የዓባይ፡ልጅ

Share:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

VK Russian online social media and social networking service
Categories