Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the matomo domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-includes/functions.php on line 6131
የግብፅ ብርቱካን - የዓባይ ፡ ልጅ
Deprecated: Creation of dynamic property OMAPI_Elementor_Widget::$base is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/optinmonster/OMAPI/Elementor/Widget.php on line 41

የግብፅ ብርቱካን

እስሌማን ዓባይ ~ የዓባይ:ልጅ

የዓባይ ውኃ ነገር አሁንም “ወይ ዓባይ..!’ የሚያስብል ነው..። እንደማንኛውም የአለም ሀገር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በግብፅም የሙቀት መጨመር ያስከተለ ይሁን እንጂ ለብርትኳን ምርቷ ግን በተቃራኒው እጅግ ጠቃሚ ነው የሆነላት። ለብርትኳን ጣፋጭነት፣ ለከለሩ ማማር እና በቶሎ ምርት እንዲሰጥ ሞቃታማ አየር በእጅጉ ነው የሚስማማው። ለምሳሌ ከ 37 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ ሙቀት ላይ የብርቱካን ተክል እድገት በእጥፍ የሚፈጥን ይሆናል።(ከአንድ ጥናት ላይ እንደተመለከትኩት)። በዚህም የግብፅ ብርቱካን ተመራጭነት ከአለማችን ግንባር ቀደሙ ሊሆን ችሏል። እዚህ ላይ አንድ መሰረታዊ ነገር መሟላት አለበት። ብርቱካን ሙቀት የመውደዱን ያህል የሚቀርብለት ውኃ ደግሞ ከሙቀቱም በበለጠ ምርታማነቱን የሚወስን ነው። በ 2022 የነበረው የአየር ንብረት ለውጥ(ሙቀት መጨመር) ለግብፅ የብርቱካን ምርት ማደግ በጣም  ጠቃሚ ነበር ያለው የሀገሪቱ … ነው። ምክንያቱም የግብፅ እርሻ በነዲድ በረሃ ውስጥ ቢሆንም የውሃ አቅርቦት ችግር አልነበረባትም። ዓባይ ወደ ፈርኦኖች የምድር ቃጠሎ ተጉዞ ጣፋጩን ፍሬ የሚለግስ ፀጋ ስለሆነላቸው።(እነሱም ወጥረው ነው የሚሰሩበት)።

ግብፅ በዚህ የምርት ዘመን 3.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብርቱካን እንደምታመርት ሪፖርት ተደርጓል። ይህም 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ከነበረው ያለፈው አመት ምርቷ የ 20 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ሪፖርት ተደርጓል። አሁንም በ 15 በመቶ ጭማሪ ምርታማነቱ እያደገ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ግብፅ ብርቱካን የተከለችበት የበረሃ መሬቷ 172,200 ሄክታር ደርሷል። ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር የ 4.5% ብልጫ ያለው ነው።) ይህ በተለይም የናይል ውሃ ገብ በሆነው በረሃማ ሸለቆ ላይ አሮጌ የአትክልት ቦታዎችን በአዳዲስ የፍራፍሬ ዛፎች ለመተካት እያደረገችው ባለው ጥረት የተመዘገበ ነው። ይህ በግብፅ በረሃ የለማ የብርቱካን እርሻ የአንድ አመት የውሃ ፍጆታው እስከ 5 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ነው።

የብርቱካን ኤክስፖርቷ (በ2022–23) የ 30 በመቶ ጭማሪ እንደሚያሳይ የተገለፀ ሲሆን መጠኑም 1.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነው ይላል የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት። አስሩ የግብፅ ኤክስፖርት መዳረሻዎች ሩሲያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ባንግላዲሽ፣ ህንድ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት እንግሊዝ፣ ቻይና፣ ማሌዢያ እና ኦማን ናቸው።

ግብፅ ወደ ውጭ የላከችው የብርቱካን ጭማቂ (በ 2022) 2,869 ሜትሪክ ቶን ሲሆን የቀደመው አመት ኤክስፓርቷ 1,897 ሚሊዮን ቶን ነበር

ግብፅ የአለማችን ቁጥር አንዷ ብርቱካን ላኪነት ደረጃዋን ለሁለተኛ ተከታታይ አመት አስከብራለች። ተፎካካሪዋ ስፔንን በመብለጥ። ግብፅ ካመረተችው 1.8 ሚሊዮን ቶን ብርቱካን 1.68 ሚሊዮኑን ለውጭ ገበያ አቅርባለች። ይህም የ 1 ቢሊዮን ዶላር ምንዛሬ ያስገኘላት ሆኗል፤

✍️ Esleman Abay
#ዓባይ #የዓባይልጅ #ኢትዮጵያ #بحيرة_أفريقيا #Ethiopia #GERD #Egypt

References: ⏬

https://www.agrifarming.in/orange-farming-project-report-cost-profit

https://growgreatfruit.com/how-much-water-is-enough/

https://issuu.com/tradologieb2b/docs/egypt_the_world_s_biggest_exporter_6de5a4c3288b40

Share:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

VK Russian online social media and social networking service
Categories