
ግብፅ ውስጥ ለሚገኘው አስዋን ግድብ ውሀ የሚያቀርብ ሌላ ግድብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰራ ታቅዶ ነበር
በአሜሪካን ሀገር መኖርያቸውን ያደረጉት የምህንድስና ባለሙያው እና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥናቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ የሚታወቁት አቶ ሲሳይ አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው መረጃውን የተናገሩት።
እንግሊዝ ግብፅ ውስጥ በስፋት ጥጥ ታመርት ነበር፤ ያ ጥጥ ወደ እንግሊዝ ሄዶ የሱፍ ጨርቅ ይመረትበት ስለነበር፤ የአባይ ውሀ ፍሰት እንዳይቀንስ ትሰጋ ነበር፡፡ በግብጽ እና በሱዳን ለከፈቷቸው ኢንዱሰትሪዎች ቋሚ የጥጥ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግም ቋሚ የውሀ አቅርቦት ያስፈልግ ነበር፡፡ አስዋን ግድብ እንደተገነባ፤ እድሜው እንዲረዝምና በቋሚነት ውሀ እንዲያቀርብ እንግሊዞች ኢትዮጵያ ውስጥ ግድብ እንዲገነባ አቋም ይዘው ነበር፡፡ አንደኛ እንደ ድርቅ ያለ የችግር ጊዜ ሲመጣ መጠባበቂያ ግድብ ውሀ እንዲለቅ ነበር የታሰበው፡፡
ሀይለኛ ጎርፍ ቢመጣም፣ እየበረደ ሱዳንን አልፎ ወደ ግብፅ ይደርሳል ተብሎ ታስቦ እንደነበር ነግረውናል፡፡
ሌላው እንግሊዞች በወቅቱ አስበውት የነበረው፤ በትነት ውሀ እንዳያጡ ይሰጉ ስለነበር፤ ከጣና ሀይቅ በመጥለፍ በቱቦ አድርጎ ውሀውን መውሰድ ነበር፡፡
ታዲያ የህዳሴ ግድቡ ለግብፅ ያለውን ጠቀሜታ እንግሊዝም ቀድማ ያስገነዘበቻት ሀቅ ሆኖ እያለ ቅዠትን መንገዷ አድርጋለች።
- Africa at a crossroads: geopolitics and power, the global tax justice roadmap
- Why Russia-Africa Youth Public Forum Promises Rapprochement & Enhanced Cooperation
- The Occupation of Rafah Crossing and the Hypocrisy of Sisi’s Policies
- People’s Dam, GERD-Diplomacy Dead End, and Egypt’s Red Line for a Non-Deferent Ethiopia

