
Esleman Abay የዓባይ፡ልጅ እስሌማን ዓባይ
በዋሽንግተን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መሰል ታጣቂዎችን መደገፍና እንደ ጫና ካርድ መጠቀም ድፍን ዓለም ያወቀላት የጣልቃገብነት ስትራቴጂ ነው። ህወሃት በአሜሪካም ሆነ በሌሎች የሽብር ድርጅት ጥናት ተቋማት ዌብሳይቶች ውስጥ Third Tier Terrorist ድርጅት ተብሎ የተቀመጠ ነው። ይህን አሸባሪነቱን እንደመዘገበች ነበር አሜሪካ ደርግን ለመጣልና ህወሃት ተላላኪ መንግስት ይሆንላት ዘንድ የፈቀደችው። አሜሪካ ከህወሃት በተጨማሪ አልሸባብን ቦኮ ሀራምን እንዲሁም በሶሪያ አልቃኢዳን አጋሯ አድርጋለች። ይህ በተጨባጭ መረጃ የተረጋገጠ ሀቅ ሲሆን ስለጉዳዩ የተጠየቁት ባራክ ኦባማ የሶሪያ አልቃይዳ በሺር አልአሳድን ለመጣል የሚታገል ለዘብተኛ አማፂ moderate rebels ናቸው” ሲሉ ነው ቃሉን ለወጥ አርገው ያመኑት።
“How Boko Haram Become a Silver Lining for Emperialism in Africa” በሚል የተሰናዳ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ ሌላው ማጠናከሪያ ነው። በናይጄሪያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የምእራባዊያን ኢምፔሪያሊዝም በናይጀሪያ እግሩን ለመትከል የበረከት ያህል ነበር የሆነለት ይለናል። አሜሪካ መራሹ ኔቶ በሊቢያ የፈፀመውን ጦርነት ተከትሎ ፈረንሣይና አሜሪካ በማሊና ኒጀር ይዞታቸውን አስፋፉ። “ይህም ከሰሃራ በታች ያለውን ትርምስ ወለደ።” ሲል ሁኔታውን ይገልፀዋል ጥናታዊ ፅሁፉ። በወታደራዊ ደረጃ አፍሪካ በፍጥነት የአሜሪካን መለዮ የለበሰች አህጉር እየሆነች ነው። በሰሜናዊ አፍሪካ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች፣ በአሜሪካ ቦምቦች የደለቡ አሸባሪዎች፣ በምእራባዊያን ገንዘብ ያበጡ ነፍሰ በላዎች እስከ ናይጄሪያው ቦኮ ሃራም ያሉ ቡድኖች የሰለጠኑት በአሜሪካ ልዩ ዘብ ወታደሮች ነው” ሲል አስቀምጧል ፅሁፉ።
ያኔ 300 የናይጄሪያ ልጃገረዶች ሲታገቱ አሜሪካ “ሰብአዊ” ጣልቃገብነት በሚባለው ዘዴዋ እጇን ለማስገባት የወሰደባት ከወር ያነሰ ጊዜ ብቻ ነበር፤ ይህም በርካቶች በመገረም ቅንድባቸውን ከፍ ያደርጉ ዘንድ ምክንያት ነበር። የሚገርመው አሜሪካ መራሹ AFRICOM ከናይጄሪያ ወታደራዊ ሃይል ጋር የነበረው ልዩ ግንኙነት በሚስጥር ቆይቶ save our girls በሚል አለማቀፍ ዘመቻ ሲጀመር ግን ነገሮች ይገላለጡ መጀመራቸው ነበር።
ከዚህ ወቅት ጀምሮ AFRICOM የናይጄሪያውን ሬንጀርስ ሻለቃ የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ሲያሠለጥን እንደቆዬ በድንገት ይፋ ሆነ። በመጨረሻም ኒውዮርክ ታይምስ ሳይቀር የአሜሪካ ጦር ከናይጄሪያ ሴቶች መታገት በፊት ለአመታት ምስጢራዊ ወታደራዊ ስልጠናና ዘመቻ ሲያደርግ እንደነበረ ይፋ አደረገ። (በተያያዥ አንድ የሚገርመኝ በናይጀሪያ የተፈፀመ ህዝባዊ ተቃውሞ ከአመታት በፊት ተደርጎ ነበር፤ ይኸውም አሜሪካ ቦኮ ሀራምን በአሸባሪነት ለመፈረጅ ረቂቅ ሰነድ ሲያዘጋጅ ናይጄሪያዊያን በተቃውሞ ቀወጡት፤ ሰዎቹ ቦኮ ሐራምን ይጠሉታል፤ “ቦኮ ሐራም በቀደደው አሜሪካ ከገባች ደግሞ የባሰ አለቀልን” የሚለው የተቃውሞው መነሻ ነበር)
▪️ የሶማሊያው ደህንነት አለቃ ስለ አለሸባብ ጥቃት
መስሪያ ቤት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር “አልሸባብ የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ የፈፀመውን ጥቃት እንዲህ በቀላሉ መመልከት አይገባም።” ሲል የተናገረውም ቡድኑ ድንበር ጥሶ ሲገባ ሌላ የሚጋልበው አካል መኖሩን በማገናዘብ ነበር።
ፋሃድ ያሲን በሶማሊያና በአፍሪካ ቀንድ እንደ አጠቃላይ የሚስተዋሉ የደህንነት ፈተናዎችን በብቃት ለመቋቋም እባለ 5 ነጥብ ምክረ ሀሳባቸውንም ያካፈሉ ሲሆን ህወሀት በሶማሊያ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ሰርጎ መግባቱ የአደጋ ዋነኛ መንስኤ ብለዋል።
አክለውም፣ የሶማሊያ ብሔራዊ የደኅንነት ኮሚቴ ጠንካራ መመሪያዎች ለማስተላለፍ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት አስፈላጊ ነው፤ እንዲሁም ከህወሓት ጋር ኔትዎርክ ያላቸው ሰዎች ከአመራሩ እና የደህንነት መዋቅሩ ውስጥ አሉ፤ እንዲመራ ማድረግ አደገኛ ነው።
የህወሃት ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር ሲዋጋ፣ አንዳንዶቹ አባሎቹ ደግሞ ከአሸባሪ አካላት ጋር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው። ከነሱ ጋር መስራት በሶማሊያና በአጠቃላይ ቀጣናው ላይ አደጋ ነው!” ፋሃድ ያሲን፣ የሶማሊያው ደህንነት መስሪያ ቤት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር
አሜሪካ አልሸባብን በአሸባሪነት ፈርጃ በአንድ በኩል ቡድኑን በተለያዩ ክንፎች እየመደበች በትጥቅ ስንቅና ስልጠና ስትደግፍ እንደነበር እንዲሁ ፀኃይ የሞቀው ሀቅ ነው። ለአብነትም የአሜሪካው ፔንታጎን የቀጠረውና ብላክዋተር የተሰኘው ወታደራዊ ተቋራጭ የሶማሊያ ሚሊሻዎችን በድብቅ መደገፉ ከ2011 ወዲህ ይፋ ሲደረግ ቆይቷል። ይህ ብላክ ወተር የተባለው ወታደራዊ ተቋራጭ በኢራቅ እና አፍጋኒስታን ታጣቂዎችን በደገፈበት ታሪኩ በተመሳሳይ ነው በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ የተሳተፈው።
አልሸባብ ከአሜሪካ ጦር ጋር ስላላቸው ድብቅ ግንኙነት Mint Press Institute ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ፣ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣን የነገሩትን በማካተት “..የባህር ላይ ወንበዴዎችን ለመዋጋት ከሚለው አላማ በተጨማሪ በፑንትላንድ ይገኝ ለነበረው የሶማሊያ አደገኛ የሽብር ቡድን ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በብላክ ወተር በኩል ከአሜሪካው ፔንታጎን ቀርቦላቸዋል..” ሲል አስነብቧል። ሚንት ፕሬስ አክሎም “አውሮፓ ህብረት የሚያሰለጥናቸው በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በወር 100 ዶላር ያገኛሉ፤ ከአሜሪካው ወታደራዊ ተቋራጭ ግን በወር 300 ዶላር በስልጠና ወቅት ሲሰጣቸው፤ ከተመረቁ በኋላ ደግሞ ደሞዛቸው በወር 500 ዶላር እንደሚቆረጥላቸው ለሚንት ፕሬስ ኢንንቲትዩት የገለፁት ሌላኛው የአሜሪካ መንግሰት ባለስልጣን ናቸው።
▪️ከአሜሪካ የቅርብ ጊዜ ስውር ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣
የአሜሪካ ልዩ ዘብ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ለመግባት በሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም አመሻሹን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ዌብሳይት ያሳወቀው። በወቅቱ የኒውዮርክ ልዩ ብሄራዊ ዘብ አባላት የሆኑ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሊሰፍሩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቁጥራቸው አንድ ሺህ ከሚሆኑት አባላቱ መካከል፣ የተመረጡ ወታደሮች የሚሰፍሩት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኬኒያ ውስጥ መሆኑ ተነግሯል፡፡ አሜሪካ ከአስራ ሁለት አመታት በፊት የአፍሪካ ቀንድን ለመቆጣጠር በሚል ጅቡቲ ውስጥ ያቋቋማቸው የሌሞኔር ካምፕ አንዱ የወታደሮቹ መስፈሪያ ሲሆን፤ በኬኒያና ሶማሊያ ግን የት ቦታ እንደሚሰፍሩ፣ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ መሆኑ ከመጠቀሱ ውጪ ቦታው በወታደራዊ ሚስጥርነት ተይዞ እንደሚቆይ ነበር የተገለፀው። ለምን የሚለውን በጋራ እናሰላስል እያልኩኝ፤
▪️ድንበር ጥሶ የመጣው አልሸባብ ቡድን በሙሉ ሲደመሰስ የምእራባዊያን ሚዲያዎች ተገቢ ሽፋን ያልተሰጡትስ ለምን ይሆን?
የዓባይልጅ #HornOfAfrica #Somalia #Somaliland #AlShabaab
ዋቢዎች 🔻
https://eslemanabay.com/united-states-in-somalia-still-at-war/
