
መከላከያ ሰራዊቱ መቀሌ ከተማን በቅርብ ርቀት ከበባ ማስገባቱን ተከትሎ የህወሓት ቡድን “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” በሆነ ውሳኔ እየፈፀመው ያለው ተግባር አሳዛኝ ነው።
የሽብር ቡድኑ በመቀሌ ከተማ እስር ላይ የነበሩ በርካታ ታራሚዎችን በመበተን በዘራፊነት አሰማርቶ ወደ በረሃ በመሸሽ ላይ መሆኑ ነው የተሰማው።
ህወሃት ይህን መሰል ድርጊት ሲፈፅም የመጀሪያው አይደለም። 2013 ዓ/ም ላይ መከላከያ ሰራዊቱ መቀሌን ከበባ ውስጥ ሲያስገባ በተመሳሳይ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በመልቀቅ በከተማው ስርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን፣ የህዝቡ ቀሪ ንብረት እንዲዘረፍና በርካቶች በማጅራት መቺ ህይወታቸውን እንዲያጡ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ይህ ህወሃታዊ ሴራ መከላከያ ሰራዊቱ ከተማ በማረጋጋት ስራ እንዲጠመድ ያለመ ሲሆን፣ ቡድኑ ለህዝብ ደንታ እንደሌለው በድጋሚ ያረጋገጠ ድርጊት ነው።
ይሁንና የመቀሌ ህዝብ የህወሃትን ሴራ በተደጋጋሚ በመመልከቱ ራሱን የማትረፍ አማራጮችን እየወሰደ ነው ተብሏል። መደበቂያ ያለው የከተማዋ ነዋሪ የሌባ ሲሳይ ላለመሆን የቻለውን ንብረት ይዞ ወደ ገጠር አካባቢዎች በመሸሽ ላይ እንደሆነ ነው የተሰማው።
#ENDF
- Africa at a crossroads: geopolitics and power, the global tax justice roadmap
- Why Russia-Africa Youth Public Forum Promises Rapprochement & Enhanced Cooperation
- The Occupation of Rafah Crossing and the Hypocrisy of Sisi’s Policies
- People’s Dam, GERD-Diplomacy Dead End, and Egypt’s Red Line for a Non-Deferent Ethiopia

