
ማሊ በፈረንሳይ የሚደገፉ NGOs ከሀገሪቱ እንዲወጡ አዘዘች
ማሊ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ተከትሎ ፈረንሳይ ለሀገሪቱ የምትሰጠውን ድጋፍ ለማቆም የወሰነችው በቅርቡ ነበር። ይህን ተከትሎ የማሊ መንግሥትም የፈረንሳይን ውሳኔ የተቀበለ ሲሆን፣ በምላሹም በፈረንሳይ ያንግስት ፈንድ የሚደረጉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች NGOs ከማሊ ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ አሳልፏል።
የማሊ መንግስት በዛሬው ዕለተ ሰኞ አመሻሽ ላይ እንዳስታወቀው ሰብአዊ በተባሉ መስኮች የሚንቀሳቀሱትን NGOs ጨምሮ በፈረንሳይ ፋይናንስ የሚደረጉ ወይም ድጋፍ የሚያገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን(መያድ) እንደሚያግድ ይፋ አድርጓል።
በርካታ መያዶች በማሊ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም በትምህርት መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ባማኮ ያሳለፈችውን ውሳኔ ተከትሎ እንደ CCFD፣ Terre-Solidaire፣ Handicap International፣ Médecins du Monde፣ እና Oxfam ጨምሮ የተለያዩ NGOs የፈረንሳይ ዕርዳታ ማቋረጥን ተከትሎ የሚወሰዱ ርምጃዎች የሚመለከታቸው ይሆናል።
የፈረንሳዩ የዜና አውታር France 24 ጉዳዩን ሲዘግብ የማሊ መንግስትን “ጁንታው አመራር” በሚል ርዕሰ አንቀፅ ሲገልፅ ተስተውሏል።
#የዓባይልጅ
