ፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ላይ ከሽፏል፡ ግብፃዊው የአረብ ሊግ ዋና ፀኃፊ ያዘነቡት ወቀሳ

https://english.aawsat.com/home/article/3702786/ethiopia-prepares-3rd-gerd-filling-aboul-gheit-slams-un-security-council


የዓባይ፡ልጅ

የአረብ ሊግ ዋና ጸሃፊው ግብፃዊ አህመድ አቦል-ገይት ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ልታከናውን መሆኑን በተመለከተ በሰጡት መግለጫቸው ነው አለም አቀፉን ማህበረሰብ የተቹት። የዋና ፀኃፊው ትችታዊ ንግግር ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ጣልቃ የከተተቻቸው አለማቀፍ አካላት ውጤት አልባ መሆናቸው ለግብፅ የውድቀት ምክንያት ነው የሚል ምልከታ የሚንፀባረቅበት ነው።
ግብፃዊው አቡል ገይት ከመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጀምሮ መላው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብፅን መታደግ ላይ ከሽፏል ሲሉ ነው የተደመጡት።

“የፀጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ሰላምን እና ደህንነትን የማስጠበቅ ሃላፊነት አለበት።” ሲሉ አቦል ገይት ከትላንት በስቲያ እሁድ እለት በቴሌቭዥን በተሰራጨ መግለጫቸው ወቀሳቸውን ያሰሙ ሲሆን “በግብፅና በሱዳን የሚኖሩ ከ150 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የፀጥታው ምክር ቤትና አለም አቀፉ ማህበረሰብ የወሰደው ምንም አይነት ርምጃ ባለመኖሩ አዝናለሁ።” ማለታቸውን አሽራቅ አል-አውሳት አስነብቧል።

የአረብ ሊግ ዋና ፀኃፊው ሀገራቸው “ግብፅ 55 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚገመተውን የናይል ውሃ ድርሻዋን አሳልፋ አትሰጥም።” ብለው “የካይሮ አመታዊ የውሃ ኮታ ላይ ተጽእኖ ሳታደርግ ህዳሴ ግድቡን ሙሌት የምታከናውን ከሆነ አዲስ አበባን ለማግባባት ምንም አይነት የውጭ አካላት ጣልቃ ገብነት ላያስፈልግ ይችላል።” በማለት ቁጭት አዘል አስተያየት ሰጥተዋል።
አቦል ገይብ ከዚህ ባሻገር “በውሃ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ውሃን መልሶ በመጠቀምና ፣ዘመናዊ የመስኖ መሳሪያዎችን በማሻሻል እንዲሁም በከርሰ ምድር ውሃና ጠብታ መስኖ ላይ አተኩረው ይሰሩ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

አሽራቅ አልአውሳት በዘገባው “የፀጥታው ምክር ቤት በወርሃ መስከረም አጋማሽ ሦስቱ አገሮች በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር የሚደረገውን ድርድር እንዲቀጥሉ መጠየቁን እና “በግድቡ አሞላልና አሰራር ላይ በተገቢ የጊዜ ሰሌዳ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ” እንደሚያስፈልግ ማሳሰቡን አስታውሷል።
የዓረብ ሊግ በግድቡ ጉዳይ ባለፈው አመት የግብፅና ሱዳንን አቋም ደግፎ መግለጫ ማውጣቱን ጨምሮ ያወሳው አሽራቅ አልአውሳት፤ በወቅቱ ኢትዮጵያ ያልተገባ በነበረው የአረብ ሊግ ጣልቃ ገብነት ቁጣዋን መግለጿንና የሊጉን መግለጫም ውድቅ እንዳደረገች አስታውሷል።

የአረብ ሊጉ ዋና ፀኃፊ የስድብ ጭብጥ ሲጠቀልል፦
“በዓባይ ጉዳይ በፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲሁም ምእራባዊያንና የፀጥታው ምክር ቤት ተቧድነው ጥረት ቢያደርጉም የኢትዮጵያዊያን አንድነትን ማሸነፍ ሳይቻለው ቀርቷል።”

#السودان #اثيوبيا #ابنالنيل #የዓባይልጅ

Arab League Secretary-General Ahmed Aboul Gheit criticized the international community as Ethiopia is expected to start the third phase of filling the Grand Renaissance Dam’s reservoir during the upcoming rainy season.

Aboul Gheit said Sunday the international community, starting with the United Nations Security Council, has “failed” Egypt and Sudan.

The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) is set to be the largest hydroelectric dam in Africa but has been a center of dispute with downstream nations, Egypt and Sudan, ever since work first began in 2011.

Cairo has reiterated its demand that Cairo, Addis Ababa and Khartoum reach a legally-binding agreement to fill and operate the dam.

Ethiopian officials have recently stated that the third filling will take place in August and September.

“The Security Council claims that it is responsible for maintaining international peace and security,” Aboul Gheirt said in televised statements on Sunday.

However, he expressed regret that it hasn’t acted to protect more than 150 million people in Egypt and Sudan.

He further stressed that Egypt will not give up any of its share in the Blue Nile waters, estimated at 55 billion cubic meters.

Aboul Gheit said if Egypt succeeds in persuading Ethiopia to fill the dam reservoir at a reasonable amount and without affecting Cairo and Khartoum’s annual quota, then they will not have to resort to any external political measures.

He urged relevant authorities to work on expanding water circulation, improve modern irrigation tools, rely on groundwater and work on drip irrigation.

The last round of talks between the three countries in Kinshasa ended in early April 2021 with no progress made.

In mid-September, the Security Council called on the three countries to resume African Union-led negotiations, stressing the need to reach a “binding agreement on the filling and operation of the dam within a reasonable timetable.”

The Arab League has repeatedly announced its support for the Egyptian and Sudanese positions in this regard and has called on Ethiopia to consider their concerns and reach an agreement that meets the demands of all parties.

This has angered Addis Ababa, which rejected the “unwanted” Arab League intervention

https://english.aawsat.com/home/article/3702786/ethiopia-prepares-3rd-gerd-filling-aboul-gheit-slams-un-security-council

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories