ጆርዳን ለልጇ ያወጣችው ስም ነው። መንፈሳዊ ህይወት መገለጫዋ ነው። በዮርዳኖስ ወንዝ የሠየመችው ልጇ ከ 8 አመት በፊት በሌላ ነጭ ታዳጊ በጥይት ተገደለባት። “ሙዚቃው ይረብሽ ነበርና ገደልኩት” የሚለው ገዳዩ “ለምን ገደልከው?” ተብሎ ሲጠየቅ የሰጠው ዳቢሎሳዊ መልስ ነበር።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮም እናቱ ማክባት በአሜሪካ መሳሪያን በየሱቁ መሸመት እንደልብ እንዲሆን የሚፈቅደውን ህግ የምትሟገት አክቲቪስት ሆነች። ጥረቷን ቀጠለችበት። 2018 ላይ የሪፐብሊካን ሴናተር ሆና አሸነፈች። አሁንም ጥረቷን አላቆመችም።
* * *
በአሜሪካ በያመቱ 77 ሺ 603 አሜሪካውያን በመሳሪያ ይገደላሉ። በያንዳንዷ ቀንም ከ 100 በላይ ለሞት ይዳረጋሉ። ከ 200 በላይም ይቆስላሉ። በ 2017 ላይ ደሞ አሀዙ በከፋ መጠን ጨምሮ 475 ሰው በቀን ማለትም 173, 375 ሺህ በአመት ተገድለዋል።
የሚያሳዝነው ነገር የቅርብ በሆነ ሰው ተተኩሶባቸው የሚገደሉት 60 በመቶውን ቁጥር መያዙ ነው። ከ 1,700 በላይ ታዳጊ ህፃናትም በያመቱ በቅርብ ሰው በጎረቤት ወይም በት.ቤት አጋር ይገደላሉ። በተመሳሳይም በየወሩ 53 እናቶች በራሳቸው ሰው ይገደላሉ። አሁን ላይ 4.5 ሚሊዮን አሜሪካውያን ሴቶች በመሳሪያ ተመተው ከጉዳቱ ጋር በድጋፍ እየኖሩ ናቸው። ከሌሎች “ያደጉ” ከሚባሉ አገራት አንፃር የአሜሪካ ሴቶች ወዳጅ/የኑሮ አጋር በነበረ ሰው በመሳሪያ የመገደል መጥፎ ዕድላቸው በ 21 እጥፍ በላይ ነው። ከ 1000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በፖሊስ በያመቱ ይገደላሉ።
ባለፉት 10 አመታት ውስጥም ከአምስት ነፍሰ በላ መንስኤዎች ውስጥ መሳሪያ ከግምባር ቀደም ገዳዮች ውስጥ ሆኗል።
በአሜሪካ የመሳሪያ ቁጥጥር በህግ እንዲገደብ በቀደሙት መሪዎች ወቅትም ሲጠየቅ የቆየው አቤቱታ አሁንም መልስ አላገኘም። ትራምፕ በምርጫ ዘመቻው ወቅት ቃል ገብቶ ነበር። አላደረገውም። ሰሞኑንም ተፎካካሪው ጆን ባይደን የትራምፕን ቃል አለማክበር ጠቅሶ ወርፎታል። ታዲያ ትራምፕ ሆዬ ምን ቢል ጥሩ ነው? “bIden is against the God and against the Gun” …ተመልከቱት…!
ዶላሩ ላይ ያለው “In God We Trust” መፈክር “In Gun We Trust” ቢባል አይሻልም…!?
by the way, ችግሩ እኛም ጋ አለ። መሳሪያ በገፍ፣ ገበያው በገፍ፣ ዋጋው ሰማይ፣ ሞቱም በብዛት ሆነበል። ከምንም በላይ ግን ወገን ወገኑን በመግደል ረገድ የኛም አሳፋሪው አሳዛኝ ሀቅ እየሆነ ነው።
በመሳሪያና ጉልበት አንመካ! በፈጣሪ’ንጂ!
በመጨረሻም ዘንድሮ 25 ዓመቱን ይይዝ ለነበረው ልጇ ጆርዳን ሴናትሯና የመሳሪያ ቁጥጥር ተሟጋቸበ ለልጇ ዕለተ-ልደት ላይ ከፃፈችው ልብ የሚነካ ሀዘናዊ ደብዳቤ ልብ ውስጥ ABC በድረገፁ ካሰፈረው ውስጥ የቀነጨብኩትን አሰፈርኩ……
I never got to kiss you goodbye. I never got to give you one final hug, ………..
…………We never celebrated your 18th or 21st birthday because you were stolen from me at just 17 years old.”
…..Today would have been your 25th – and I still miss you every single day,
……..she continued. “If you were still here, I’d tell you how proud I am of the person you’ve become –
………You live on through me. And I live on because of you,” she said. “Today, you would have been 25 years old. Happy birthday, Jordan. I miss you. I love you so much.”