=War Reporting and National Interest
የCNN ጎምቱዋ ክሪስቲን አማንፑር፦ ‘በጦርነት ዜና ላይ አገራዊ ጥቅምን ካስቀደምን በኋላ ነው ሚዛናዊነትና ገለልተኝነትን ታሳቢ የምናደርገው’ ማለቷን የሚጠቅስ ፅሑፌን ካነበበ በኋላ ነው የሙያ አጋሬ ኤሊያስ መሠረት ይህን ያለው። በርግጥም የአማንፑር ንግግር በብዙዎች የሚታወስ እንጂ የኔ ፈጠራ አይደለም። “..Objectivity doesn’t mean neutrality. Objectivity means getting all sides of the story. When you mistakenly believe objectivity is neutrality, that means you start to try to make a false factual and moral equivalence. You then become an accomplice.”
አማንፑር በጦርነትና አደጋ ቦታዎች እየተገኘች በርካታ ዘገባ ሰርታለች። 1994 ላይ ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ “When there is a war, there is Amanpour” ብሎ እስኪፅፍ ድረስ…።
ታዲያ በቦሲኒያና በሌሎችም ጦርነት ዘገባዎቿ ላይ “ስብዓዊ ርህራሄ ይታይብሻል፤ ሙያዊ ገለልተኝነቱስ?” ሲሉ ለጠየቋት ነበር ከላይ ያስቀመጥቁትን ምላሽ የሰጠችው።
ለዚህ አቋሟ የገፋት ምክንያትም፣ ለጦርነቱ መከሰት ብሎም ለተመለከተችው አሳዛኝ ሰቆቃ ‘በህይወትና ደም የሚነግዱ ፖለቲከኞች የችግሩ አካላት ሆነው ተጎጂዎቹ ግን ንፁሃን መሆናቸውን መታዘቧ ነው። ሰብአዊ ርህራሄ promote መደረግ ያለበት ነውና።
አማንፑር ይህን አቋሟን አንዴ ብቻ አይደለም ብዙ ጊዜ አንፀባርቃዋለች። በጋዜጠኞች ምረቃዎች ላይ፣ በጋዜጠኝነት ሙያዊ ኮንፈረንሶች፣ የቴሌቪዥን ሾዎች ወዘተ ላይ ተናግራዋለች
( የአማንፑርን ንግግር ከዩቲዩብ ቻናሌ ታገኙታላችሁ
👉 https://youtu.be/fUmIy0O8PFg )
ኤሊያስ መሠረት ከዚህ ይልቅ ትላንት ምሽት ሲዘዋወር የነበረውን የሟች ልዩ ሃይሎች ምስል “ethiocheck” ላይ የሆነ ነገር ቢልበት መልካም በነበር ባይ ነኝ።
በጦርነት ዘገባ ወቅት ሶስት መርሆች እንዲተገበሩ ሙያው ያስቀምጣል። የግጭቱ መሠረታዊ መንስኤ፣ ግጭቱን ያባባሰውና የግጭቱ ድርጊቶች ናቸው። ከዚህ አንፃር በምቹ የስራ ግብአት ላይ ያለው ኤሊያስ ስለ ግጭቱ መንስኤ በፌስቡክ ገፁ ለማጋራት የልቦና ፈቃዱ ቢሆን ኖሮ ለአገር ወግኖ መዘገብን የሚፃረር ምላሽ ለመስጠት አይምሮውም አይፈቅድለትም ነበር ባይ ነኝ።
ኤሊያስ ለጉዳዮች የዘገባ ሽፋን የሚሰጥበት፣ የሚተውበት እንዲሁም entertain የሚያደርግበት መንገድ በርካቶችኝ ቅር ሲያሰኙ ታዝቤያለሁ። (የትግራይን ምርጫ የደገፈበት እና ህወሃት ሰሜን እዝን ካጠቃ በኋላ የገባንበትን ጦርነት “የወንድማማቾች ጦርነት” ያለበት ፖስቶቹ የቅርብ ቀናት ትውስታ ናቸው) የፅሑፌ አላማ ነገርን ነገር ካነሳው አይቀር ሁላችንም ሀሳብ እንድንሰጥበት ብቻ ነውና ሌሎች ችግሮቹን ሁሉም ሰው የሚያውቃቸው ናቸው ብዬ ልለፈው። ለኔ ግን በትልቁ የሚዲያ ተቋም AP መስራቱና የሙያ አጋሬ መሆኑ ጥሩ ጎኑን እንዳይ ያደርገኝ ነበር።
ጦርነትን አያምጣብን ነውንጂ ከመጣ በኋላ መከላከያችንን እንደ ጋዜጠኛም promote ባደርግ ከአገር ጥቅም አንፃር ጉዳቱ ምን ላይ ይሆን? መከላከያ ሰራዊታችን በሚያደርገው የጦርነት ዘመቻ ላይ አገራዊ ጥቅምን ታሳቢ አድርገን መዘገብ የተለመደ ነው፤ መሆንም አለበት የሚለው ግልፅ አቋሜ ነው። ኤሊያስ ለፅሑፌ “አማንፑር አላለችም” በማለት መቶ በመቶ ደምድሞ ምላሽ መስጠቱ ምንም ማለት አይደለም። “እጅህን ከሚዲያ ላይ አንሳ” የሚል ማሳሰቢያው ግን ገርሞኛል! ማነው እጁን የጫነው? የግል አቋሙ የሚንፀባረቅባቸው የኤሊያስ ፖስቶች ብዙ ሆነው ሳለ ራሱን እንደ ፍፁም ቆጥሮ ሌላውን መንቆሩ ‘እጁን በጋዜጠኛውና ጋዜጠኝነት ላይ አሳርፏል” ያሰኛል። “አቶ ኤልያስ እግርህን ከዓባይ ልጅና ከጋዜጠኝነት ላይ አንሳ !”
እኔ በዚህ ሶሻል ሚዲያ ለብሽሽቅ የምፅፍ ብሽቅ አክቲቪስት ሳልሆን ለአገር ጥቅምና ለአንድነቷ መጎልበት በማይመች ሁኔታ ላይም የተቻለኝን መረጃ የማካፍል አፍቃረ-ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ነኝና። በመሰል ነቆራዎች አላፈገፍግም። እንደውም አጠናክረዋለሁ’ንጂ።
ኤሊያስ ሆይ ” አለማቀፍ ጋዜጠኛ” ነኝ ብለህ ራስህን ጠርተህ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሉ ወጣቶች ላይ የጀመርከውን ሴራ አቋርጥ፤ ይቅርታም ጠይቅ። እኔ ያንተን የአመት ዘገባ በ document analysis ዋጋህን ማስቀመጥ እንደምችል ስነግርህ በትህትና ነው።
ለኢትዮጵያ ጥቅም ወግኜ እዘግባለሁ ማለቴ፤ አማንፑር ባትለንም፣ BBC, CNN እና Aljazeera ወዘተ ባያደርጉት እንኳን አቋሜ ይኸው “የአገር ጥቅም ቅድሚያ የሚል” ነው።
የማከብረው ሙያዬ ከአገሬ በታች ነውና!