ሶሻል ሚዲያ የዘመኑ ባቢሎናዊ ግንብ▪️ Social Media – New Tower of Babel

የዓባይ?ልጅ

አዲስ:ዘመን
?ቋንቋችን የሚታከምበት
?የናምሩድ ግንብ (ሳይሆን)
?የኑህ መርከቦች የምንገነባበት

ቃል የቁስ-አካል መሰረት፤ ቃል የሚሸከመው ፅንሰ-ሀሳብ አለም ላይ የሚሆነውን ክስተት ለበጎም ሆነ ለጉዳት ይሆን ዘንድ ተፅዕኖ የሚያሳድር ረቂቅ ጉልበት…።
ንግግር ከሐሳብ ከልቦና እና አይምሮ የሚወለድ፤ ለምናከናውነው ተግባር ለአንድነትና ፍቅር ዋና ጥሬ እቃው ነው። ዋልታ-ረገጥነት የሚፈጠረው ልባችን ላይ የምንፀንሰው ቃል በሚይዘው ስሜት ነው። ይህን ተከትሎ በሚንሸራሸር የዜጎቿና የልሂቃን የሐሳብ መስተጋብር ሀገር የምትታነፅበት ጡብ የሚጠረበው። ለዚህ ሁሉ መሰረት ተግባቦት ነው። ተግባቦት ሲኖር ከባቢሎን ውድቀት ያተርፋል። የተበላሸ “ሀሳብ የቋንቋችንን መልክ ይወስናል። በተመሳሳይ ቋንቋም አስተሳሰብ ይበላሽ ዘንድ መንስኤ ሊሆን ይችላል”።
መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረው የባቢሎን ግንብ Tower of Bebel(600BC ) …። ባቢሎናዊያን ከፈጣሪ ደረጃ ለመገኘት በሚል ትልቅ ህንፃ ለማነፅ አሰቡ። በንጉስ ናምሩድ ትእዛዝም ግንባታውን ጀመሩ። በሁሉም ስፍራ የሚገኘው ፈጣሪ ሞኝነታቸውን ተመለከተና ስለ ትዕቢታቸውም ቋንቋቸውን አደበላለቀባቸው። ድንጋይ ሲል እንጨት፣ ኖራ ሲል ውሃ እየተቀባበሉ ስራውን ማስኬድ ተስኗቸው ተበታተኑ።
የዘመናችን የባቢሎን ግንብ Tower Of Babel ማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል። የማህበራዊ ሚዲያው ባቢሎን ግንብ ያመጣው የተግባቦት መደበላለቅ ዓለም አቀፍ መልክ ኖሮት በሀገራችንምም ስር እየሰደደ የመጣ ስጋት ሆኗል።

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለተዛባ መረጃ፣ በትንሹም ቢሆን መጋለጥ፣ ንቃተ ህሊናችን ላይ ሳናውቀው ጉዳት ይፈጥርብናል። የተዛባ መረጃ Disinformation በሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ የተደረገ ጥናት፤ 233 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ከአምስት ደቂቃ በታች ለሆነ ጊዜ ለሀሰተኛ መረጃዎች እንዲጋለጡ ተደርገው የተገኘው ውጤትም ያንኑ የሚያስረግጥ ነው የሆነው። የተዛባ/ሀሰተኛ መረጃ በምክንያታዊነትና በውሳኔ አሰጣጥዎ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። ደካማ የማመዛዘን ችሎታ ያመጣል። የአእምሯችን የአስተሳሰብ ስሪት ሆኖ ያጋጠሙን የተሳሳቱ መረጃዎች በተጨባጭ መረጃ እርማት ቢደረግባቸውም አእምሯችን ብዙውን ጊዜ ወተሳሳተው መረጃ ማዘንበሉን ይቀጥላል።
በዚህ ተጨባጭ ውስጥ ሆነን ለችግራችን መፍትሄ አይደለም – ችግሩን እንኳን ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል።
አሰው በአእምሮው አቋም የያዘበትን አተያይ፣ አቋም ሁሌ “ትክክል ነው” ይላል። የሱን ተመሳሳይ የሚያራምዱት ብቻ “ልክ ናቸው”፤ ሌሎቹ ግን “ስህተት” የሚል Confirmation-bias የሚባለው ስነልቡናዊ ችግር ከማህበራዊ ሚዲያው አሉታዊ ተፅዕኖ ጋር በጣም ተንሰራፍቷል። ይህ ችግር የተጠናወተው ሰው ስህተቱ በጉዳዩ ጠበብት ቢነገረውም እንኳን አይቀበላቸውም፤ የምርምር ግኝት ብታቀርብለትም መስሚያው የተደፈነ ነው።

የዲጂታል ቴክኖሎጂው algorithm ችግሩን ያባባሰው ሲሆን ፌስቡክም ሆነ ጉግል ቀደም ሰል በጎረጎርካቸው ፣ react ያደረከውንና ያጋራኸውን ይዘት ይመዘግባል፤ በቀጣይ መሠል ይዘት ከየትኛውም አለም ሲለጠፍ ወዳንተው ያመጣልሃል። ለማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎች ትልቅ ገበያ፣ ላንተ ግን Confirmation-Bias በሽታን የሚያተልቅብህ መዘዝ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው። የሚገርመው ደግሞ ከ71 በመቶ በላይ የሶሻል ሚዲያ አጀንዳዎችና ይዘቶ ከህዝቡ ችግር ጋር የማይገናኙ መሆናቸውን ጥናቶችን ማስቀመጣቸው ነው። የአጀንዳዎቹ ኢ-ፋይዳቢስነት መብዛት ሳያንስ ለምንሻው አገራዊ ለውጥ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከዚህ ኢ-ምክንያታዊ የሶሻል ሚዲያ ኢኮ-ቻምበራዊ(የተቧድኖ) ጩኸት አለማለፉ ነው። ሶሻል ሚዲያ መረጃን ተደራሽ፣ የባለስልጣናትን ችግር አደባባይ ለማውጣትና ተገቢ የለውጥ ጥያቄ ለማንሳት ማስቻሉ ነው ጥቅሙ። ይህ ብቻ ግን ችግር አይቀርፍም ለውጥን እውን አያደርግም። ጥያቄዎች ወደ ለውጥ የሚያሻገሩት በመንግስትና በህዝቡ መካከል ያሉ ሲቪክ ተቋማት የዚሁ አካል ሆነው በሚያስቀምጧቸው ቀጣይ ተግባራት ላይ ዜጎች ከሶሻል ሚዲያ ተሻግረው መሬት ላይ የሚወርድ ሚና ከተጫወቱ ብቻ ነው። እኛጋ አጀንዳዎች ከህዝብ ጉዳይ ይልቅ ከኢሊት ግለሰቦች ፍላጎት ብቻ ይመነጩና፣ በጥቂት የፌስቡክ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንደ አዋጅ ተደንግጎ ብዙሃኑም በዚህ ቀኖና ይነዳበታል ። ከዛማ…ቼ-በለው! ይጀመራል። የታገልን ይመስለናል። …ላይክ፣ ሼርና በ confirmatin-bias ውግንና የተጠለፈ ኮመንት በ echoe chamber ተቧድኖ መጮህ ብቻ። ለዚህም ነው ከ 75 በመቶ የሚበልጡ የሶሻል ሚዲያ የለውጥ እንቅስቃሴወቀች (ክሊክቲቪዝም) አላስፈላጊ ዋጋ አስከፍለው ሳይሳኩ የሚቀሩት፤ እንደ ጥናቶች። አክቲቪዝም በአኖኒመስ አካላት አይነዳም፤ የምክክር መድረክ ያለው፣ በጥናትና ምርምር ግኝቶች የሚመራ፣ ማህበረሰቡ በሚያውቃቸውና መሬት ወርደው በሚንቀሴቀሱ አካላት የሚመራ ቢሆን’ንጂ። Echoe-Chambers ከሚባለው (የተቧድኖ) ጩኸት ራሳችንን እንጠብቅ! confirmation-bias የስነ-ልቡና መናጋት ነውና ከዚህ ስናገግም ነው ወደ ውይይትና መግባባት ጉዞ መጀመር የሚቻለው፤ አገሌ ጥሩ! እገሌ ቀሽም! ማለት የምንችለው።

ሌላ ጥናት እንዳተተው ደግሞ፤ አብላጫው የማህበራዊ ሚዲያ ተቃርኖ በግልባጩ የተስማማንባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ይነግረናል። ለዚህም ነው በሁለቱም ሀይማኖቶች ቅዱሳት መፅሐፍ ውስጥ ከአርባ ጊዜ በላይ የተጠቀሰችው ሀገርህን እንድትክዳት ሲገፋፉህ መነሾውን ጠርጥር የሚባለው። ህዝብን ተሳደብ እያሉ ሲያጀግኑህ ለምን? እንድትል የሚነገርህ።
በአዲሱ አመት እርሶ የሚገነቡት ሰውን ከጥፋት ለመታደግ የኖህ መርከብን? ወይስ መበታተን የሚያመጣውን የናምሩድ ግንብ?
ሀገር የልጆቿ ግልጽና ስውር እሳቤ ነፀብራቅ ናትና ወደሚያግባባን ከፍ ለማለት የእያንዳንዳችን የልብ መቃናት አስፈላጊ ነው!
በቃ ይበለን! ተግባቦታችንን ያክምልን! ቋንቋችንን ይመልስልን!

??ዕ?ን?ቁ?ጣ?ጣ?ሽ??
እስሌማን ዓባይ 2015

Say #YesToUnity
#YesToLove
#YesToPEACE

#EthiopianNewyear2015 ??

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories