ፑቲን የነዳጅ እና ጋዝ ሽያጭ በሩብል ገንዘብ ብቻ የማለታቸው ቀመር

what Putin’s decision to replace the dollar with the ruble in Russian oil and gas sales means??
▪️የዓባይ፡ልጅ ✍️ እስሌማን፡ዓባይ

አውሮፓ ሀገራት የ700 ሚሊየን ዶላር ነዳጅና ጋዝ ነው ከሩሲያ በዬቀኑ እየገዛ የሚገኘው። ህብረቱ በየቀኑ 700 ሚሊየን ዶላር ለሩሲያ ይከፍላል ማለት ነው። ሩሲያ አሁን ላይ ሽያጩን በሩብል ካልሆነ አልሸጥም ብላለች። አውሮፓ ይህን ግዙፍ መጠን ያለው ዶላር በሩብል ምንዛሪ እንዲከፍል ተጠይቋል ማለት ነው።

አሁን ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር 90 ሩብል ገደማ ነው። ለስሌታችን አመችነት በመቶ ሩብል ብናድርገው አውሮፓ በያንዳንዷ ቀን 70 ቢሊዮን የሩሲያ ሩብል ማዘጋጀት/መቆጠብ ይጠበቅበታል ማለት ነው። ይህን ያህል የሩብል ምንዛሪ ከየት ​​ያመጡታል? ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ቀጥሎ ይመጣል። (ይህ ትንተና ከተለያዩ ፀኃፍት አተያይ፣ ከተለያዩ መንግስታዊ መግለጫዎችና የምርምር ተቋማት ጥናታዊ ዳታዎች ማጠናከሪያነት የቀረበ ነው። አንዳች ምልከታን የሚፈነጥቅ ሆኖ ስላገኘሁት አጋርቻችኋለሁ።)

በፑቲን አዲሱ የኢነርጂ ግብይት ውሳኔ መሰረት አውሮፓ ኅብረት የሩሲያውን ሩብል በዶላር ወይም በዩሮ ገንዘብ ለመግዛት ይገደዳል። ይህን ግዙፍ የሩብል መገበያያ ህብረቱ ከየትም ሊገዛው አይችልም። ከሩሲያ በስተቀር። ስለዚህ ጉዳይ ስናወራ አውሮፓውያን ሩብልን ከምንጠቀም የሩሲያ ነዳጅና ጋዝ ይቅርብን ቢሉስ? የሚል ጥያቄ ምናልባት ከተነሳ ቀጣዮቹን ቁጥሮች መጠየቅ ትችላላችሁ።

የኢነርጂ ኢንተለጀንስ ተቋሙ ጄይሚ ኮንቻ፣ የውል ማቋረጥ ካሳን ሳይጨምር በ2021 የታየውን አማካኝ ዕለታዊ ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አውሮፓ የሚሄደው የሩሲያ የጋዝ ቧንቧ ሙሉ በሙሉ መቋረጥ የሩሲያው Gazprom በቀን ከ203 ሚሊዮን እስከ 228 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያሳጣው ስሌቱን ያስቀምጣል።

እገዳው በዚህ ሁኔታ ለሦስት ወራት የሚቆይ ቢሆን (ሚስተር ፑቲን ፀደይ ወቅት ላይ ከታየው የጋዝ ፍላጎት መቀነስ ጋር ጋር የሚያጡት ሽያጭ ወደ 20 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ይደርሳል። ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ማጣት በኢነርጂ ላይ ለተማከለው የሞስኮ ኢኮኖሚያዊ-ጂኦፖለቲካ ትልቅ ውድመት በሆነ ነበር። ነገር ግን ፑቲን ዛሬ ላይ በማዕከላዊ ባንካቸው 600 ቢሊዮን ዶላር የመጠባበቂያ ሪዘርቭ አከማችተዋል። ከምእራባዊያን የሚሰነዘር የኢኮኖሚ አደጋ በቀላሉ ለመቋቋም ወሳኙን ጋሻ አስቀድመው ነበር ፑቲን ያዘጋጁት።

[አውሮፓ ህብረት 70 በመቶው ኢኮኖሚ የቆመው ከነዳጅና ጋዝ/ኢነርጂ ተመርኩዞ መሆኑን እዚህ ላይ ያስታውሷል።]

ወደተነሳንበት ነጥብ እንመለስ። ምን ነበር ያልነው..? አዎ.. አውሮፓ ኅብረት የሩሲያውን ሩብል በዶላር ወይም በዩሮ ገንዘብ ለመግዛት ሲገደድ፤ ይህን ያህል የበዛ የሩብል መገበያያ ከየት ያገኛል? ብለን ነበር። ከሩሲያ ማእከላዊ ባንክ ካልሆነ ከየትም አያገኘውም።

በዚህ ጊዜ አውሮፓ ህብረት ሩብል በዶላር ወይም ዩሮ ለመሸመት የሩሲያውን ማዕከላዊ ባንክ ሽጥልኝ ሲል መጠየቅ አለበት ማለት ነው። ይህም ሩሲያ የሚኖራትን የሃርድ ከረንሲ መጠን ወደሰማይ ያሳድገዋል።

ሩሲያ ይህ ስሌቷ ሰርቶላት አውሮፓ በሩብል መገበያየት ከጀመረች፤ እጇ ውስጥ ያስቀመጠችው ሌላኛው ካረሰታዋን ትመዝዘዋለች። ይህኛው ካርታ አውሮፓ ህብረትን በመዳፏ ውስጥ መክተት የሚያስችላት ነው። በዚህኛው ውሳኔ ሩሲያ ገንዘቧ ሩብል በዶላር እና ዩሮ አልሸጥም ትላቸዋለች። የሩሲያው ማዕከላዊ ባንክ ከስዊፍትና አለማቀፍ ግብይት በምእራባዊያን መታገዱ አሰራራቸውን ለዬቅል አድርጎታል የሚለው ምክንያት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። የሩሲያው ማዕከላዊ ባንክ በዚህ ጊዜ ሩብል ለአውሮፓ የምሸገው በወርቅ ነው ይላቸዋል ማለት ነው። ታላቁ ጨዋታም እዚህ ላይ ይጀመራል…

የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ አሁን ላይ 60 ዶላር ማለትም 600 ሩብል ሲሆን 600 ሩብል ሆነ ማለት ነው። በዚህ ስሌት አውሮፓ ህብረት 7 ቢሊዮን የሚጠጋውን ሩብል ለማሟላት በቀን ከ11 ቶን በላይ ወርቅ ለሩሲያ በዬቀኑ ሲያቀርብ ብቻ የሞስኮን ነዳጅና ጋዝ በዬቀኑ ያገኛል ማለት ነው።

ሞስኮ ይህን ውሳኔ ካሳለፈች በአውሮፓ ማዕከላዊ ባንኮች የሚገኘው የወርቅ ክምችት የሚገኘው ወርቅ ወደ ሩሲያው ማዕከላዊ ባንክ ተጓጉዞ የወርቅ ተራራ ይሰራል ማለት ነው። (አውሮፓ ከአፍሪካ የዘረፈችው ወርቅ ቢባልም ብዙ ውሸት አይኖረውም።) ይህን ተከትሎ የሩብል አለማቀፍ ተፈላጊነትን ወደ ሰማይ ይተኮሳል። በግዙፍ ወርቅ ተራራ ሪዘርቭ የተደገፈው ሩብል ተፈላጊነት ማደግ የአለም ሀገራት ለንግድ ልውውጥ ምርጫቸው የሩሲያው ሩብል ላይ ማዕከል እንዲያደርጉ ያስገድዳቸው ይጀምራል።

በዚህ የተነሳ ሁሉም ሀገሮች ግብይት ለመፈፀም ተፈላጊ የሆነውን የሩብል ምንዛሪ የግድ ይፈልጋሉ፤ ለዚህ ደግሞ ከሩሲያ ጋር በየትኛውም መንገድ የትኛውንም ግብይት ለማድረግ እድሎችን ሁሉ ማማተር ይጀምራሉ። ሩብል ገንዘብን በከፍተኛ መጠን መግዛትም ግድ ይሆንባቸዋል። ይህ ሆነ ማለት ሞስኮ በኒዮርክ ምትክ፤ እንዲሁም የሩሲያው ገንዘብ ሩብል በዶላር እና ዩሮ ምትክ የዓለም አቀፉ ግብይት ማእከል ይሆናሉ ማለት ነው።

ጓዶች! አሜሪካ መራሹ የምዕራባዊ ሀገራት ስብስብ ሩሲያ ላይ የከፈተው የኢኮኖሚ ጦርነት ለሞስኮ መዳፎች የጦር መሳሪያ ያህል ምላሽ የሚሰጣቸው ይሆን ጀምሯል። ከኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች በበለጠም ብርቱ እና አስፈሪው ሆኗል። የጀመሩት የኢኮኖሚ ጦርነት ራሳቸውን ምዕራባዊያንን ሊያወድም ተነጣጥሯል። አዲሱ የዓለማችን የሃይል አሰላለፍም እንዲህ እየተፈጠረ አይመስላችሁም?

[ፌስቡክ ስላገደኝ ቴሌግራም ላይ ታገኙኛላችሁ ⬇️ 👇
Esleman Abay የዓባይ ልጅ
Blog
https://t.me/eslemanabayy
Esleman Abay #የዓባይልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories