መፈንቅለ መንግስትና ሕዝባዊ አልገዛም ባይነት ሁለቱ አስፈላጊ ናቸው
መፈንቅለ መንግስትና ሕዝባዊ አልገዛም ባይነት ሁለቱ አስፈላጊ ናቸው ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) ኢትዮ ሰማይ 10/22/2021 ጌታቸው ረዳ 10/22/2021 መፈንቅለ መንግሥት በኢትዮጵያ አንጀት አርስ ሞጋች በታጣበት በዚህ ፈታኝ ዘመን እምዬ ኢትዮጵያ አምጣ የወለደችልንን ወጣቱ ብርቅየው ኢትዮጵያ ወዳጄ አቻምየለህ ታምሩ ስለ መፈንቅለ መንግሥት አላስፈላጊነት ያተተበትን ጽሑፍ ትናንት አንብቤው ነበር። መል እክቱ መቶ በመቶ ከእውነተኛ ስጋት የመነጨ እና እኔም ስጋቱን የምጋራው ብሆንም በሰጠው አገላለጽ ግን የማልስማማባቸው ነጥቦች አሉ። መጀመሪያ የወንድሜን አቻምየለህ እምነት ልጥቀስ። እንዲህ ይላል፡