
ካይሮ በፍልስጤማዊያን ደም እና በኢትዮጵያ ውኃዎች መሀል
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በተለይም ከካይሮ እስከ አንካራ፣ ከጋዛ እስከ አፍሪቃ ቀንድ ከሚስተዋሉ የአሰላለፍ መልኮች ጋር የሀገራት መሪዎችና የስለላ ኃላፊዎች ወደ ካይሮ ጉዞ የማድረጋቸው አንድምታ፣ ከጋዛ/ሐማስ ጉዳይ ባሻገር ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ስንስል ያላቸው ቁማሮችም ይመስላሉ —። ሰሞነኛው የግብፅና እስራኤል ‘ታንቲራ’ የካምፕ ዴቪድ ስምምነትን መንካት መጀመሩ ይበልጥ ሀገራችንን የሚመለከት ያደርገዋል። ካይሮ በዚሁ የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ወቅት ኢትዮጵያን የተመለከተው ይዘት ቁልፍ ሆኖ የተካተተ እንደነበርና በዚህም በሀገራችን የከፍታ ፕሮጀክቶች ላይ ጥቁር ጥላውን አሳርፎ ስለመቆየቱ የሚያወሳውን ታሪክ እዚጋ ልብ ይሏል…
